የዝግጅት ክፍሉ መልዕክት Message To Our Readers

28
የዝግጅት ክፍሉ መልዕክት ቀንዲል መፅሔት በህትመትና በድረገፅ ለአንባቢያን መድረሰ ከጀመረች እነሆ አንደኛ ዓመቷን አስቶጠረች።ባለፉት አስራ ሁለት ወራት መፅሔቷ በድረገፅ በየዕለቱ የተለያዩ ጦማሮችን ያሳተመች ሲሆን በሦስት ወር አንዴ ደግሞ የህትመት መፅሔቶችን በማሳተም እነሆ ለአራተኛ እትሟ ደርሳለች።ያለፉት አስራ ሁለት ወራት ለመፅሔቷ የትምህርት ጊዜያት ነበሩ።ምክንያቱም በእያንዳንዱ የህትመት ወቅት የሚታዩ ደካማ ጎኖችን ለማሻሻል ያለፉት ወራት የመፅሔቷ ጥሩ የግብዓት ጊዜ ስለነበሩ። በእርግጥ መፅሔቷ ያለ አንባቢያን ተሳትፎ ወደፊት መራመድ አትችልምና ውድ አንባቢዎቻችን በመፅሔቷ ላይ ስለነበራችሁ ያልተቋረጠ ተሳትፎ በእጅጉ እያመሰግናለን። በቀጣጥም በመፅሔቷ ላይ ያላችሁን መንኛውም አስተያየት በአድራሻችን እንድትልኩልን በአክብሮት እንጠይቃለን። የመፅሔቷ የድረገፅ አድራሻ www.kendilmagazine.wordpress.com ሲሆን በተለይ በየእለት ጦማሮች ወይም (blogs) ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቹ አንባቢያን ፅሁፎቻችሁን በየዕለቱ(በማንኛውም ሰዓት) በፖስታ ወይም በኢሜል አድራሻችን በመላክ በድህረ ገፃችን ጦማሮቻችሁን ልታሳትሙ ትችላላቹ። ውድ አንባቢያን ቀንዲል ላይ የሚወጡ ማናቸውም ፅሁፎች ሙሉ በሙሉ የፀሐፊው ሃላፊነት እንጂ የዝግጅት ክፍሉ እንዳልሆኑ አስቀድመን ለመግለፅ እንወዳለን። መልካም ንባብ! ታህሳስ፣2006 ዓ.ም(ቁ.4.ቀፅ አንድ) Message To Our Readers Kendil Magazine publishing both an online and print edition is remembering its one year of establishment. In the last twelve months the magazine could able to publish daily blogs and quarterly print editions. Our track record was source of experience both for the editorial board and, of course, to upgrade the quality of the magazine in gereral. In the last one year our readers have a great role in our magazine continuance. Hence, we want to give thanks to our readers for your contentious engagement. The magazine print edition is published and get reach in to readers once in a quarter year. On the other hand the online magazine which has daily Blogs and News can be found in the website www.kendilmagazine.wordpress.com . Any one who has the interest to blog on the magazine can send us articles so that it can be published both online and in the print magazine. Dear our readers, the messages of the articles in our magazine are the responsibility of the writers. The magazine editorial staffs are not accountable for articles in the magazine. We wish a marvellous stay to our readers. January 2014 (No.4) Kendil January ,2014 First Year No.4 1

Transcript of የዝግጅት ክፍሉ መልዕክት Message To Our Readers

የዝግጅት ክፍሉ መልዕክት

ቀንዲል መፅሔት በህትመትና በድረገፅ ለአንባቢያን መድረሰ ከጀመረች እነሆ አንደኛ ዓመቷን አስቶጠረች።ባለፉት አስራ ሁለት ወራት መፅሔቷ በድረገፅ በየዕለቱ የተለያዩ ጦማሮችን ያሳተመች ሲሆን በሦስት ወር አንዴ ደግሞ የህትመት መፅሔቶችን በማሳተም እነሆ ለአራተኛ እትሟ ደርሳለች።ያለፉት አስራ ሁለት ወራት ለመፅሔቷ የትምህርት ጊዜያት ነበሩ።ምክንያቱም በእያንዳንዱ የህትመት ወቅት የሚታዩ ደካማ ጎኖችን ለማሻሻል ያለፉት ወራት የመፅሔቷ ጥሩ የግብዓት ጊዜ ስለነበሩ። በእርግጥ መፅሔቷ ያለ አንባቢያን ተሳትፎ ወደፊት መራመድ አትችልምና ውድ አንባቢዎቻችን በመፅሔቷ ላይ ስለነበራችሁ ያልተቋረጠ ተሳትፎ በእጅጉ እያመሰግናለን። በቀጣጥም በመፅሔቷ ላይ ያላችሁን መንኛውም አስተያየት በአድራሻችን እንድትልኩልን በአክብሮት እንጠይቃለን። የመፅሔቷ የድረገፅ አድራሻ www.kendilmagazine.wordpress.com ሲሆን በተለይ በየእለት ጦማሮች ወይም (blogs) ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቹ አንባቢያን ፅሁፎቻችሁን በየዕለቱ(በማንኛውም ሰዓት) በፖስታ ወይም በኢሜል አድራሻችን በመላክ በድህረ ገፃችን ጦማሮቻችሁን ልታሳትሙ ትችላላቹ።ውድ አንባቢያን ቀንዲል ላይ የሚወጡ ማናቸውም ፅሁፎች ሙሉ በሙሉ የፀሐፊው ሃላፊነት እንጂ የዝግጅት ክፍሉ እንዳልሆኑ አስቀድመን ለመግለፅ እንወዳለን።መልካም ንባብ!ታህሳስ፣2006 ዓ.ም(ቁ.4.ቀፅ አንድ)

Message To Our Readers

Kendil Magazine publishing both an online and print edition is remembering its one year of establishment. In the last twelve months the magazine could able to publish daily blogs and quarterly print editions. Our track record was source of experience both for the editorial board and, of course, to upgrade thequality of the magazine in gereral. In the last one year our readers have a greatrole in our magazine continuance. Hence, we want to give thanks to our readers for your contentious engagement. The magazine print edition is published and get reach in to readers once in a quarter year. On the other hand the online magazine which has daily Blogs andNews can be found in the website www.kendilmagazine.wordpress.com . Any one who has the interest to blog on the magazine can send us articles so that it can be published both online and in the print magazine.Dear our readers, the messages of the articles in our magazine are the responsibility of the writers. The magazine editorial staffs are not accountable for articles in the magazine. We wish a marvellous stay to our readers. January 2014 (No.4)

Kendil January ,2014 First Year No.4 1

ቀንዲል

ቀንዲል ታህሳስ 200 6 ዓ . ም አንደኛ ዓመት ቁ . 4 / Kendil January 201 4 First Year 4th Edition

ዋና ስራ አስኪ ያጅ General Managerውቤ አለማየሁ Wube Alemayehu

ዋና አዘጋ ጆች Editors in chiefውቤ አለማየሁ Wube Alemayehuአበራ ሽፈራው Abera shiferaw

አዘጋጆች Editors ቴዎድሮስ ውብሸት Tewoderos Webishetሳሙኤል ምናሴ Samuel Menase

ሪፖርተሮች Reporters ሚሚ ሀብተማርያም Mimi Habtemareyamሃና መሸሻ Hana Mashasha

የኮምፒዩተር ፅሁፍና ፍን ብር Computer Graphicsፍቅርተ ታደሰ Fikrte Tadesseዳዊት አሰፋ Dawit Asefa

የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ዎች Coordinators ርብቃ ለማ Rebeca Lemmaሰላም ፍቅሬ Selam Fikre

የፎቶ ግራፍ ባለሙያዎች Photographersቢንያም ሀይሌ Biniame Haileጋሻው መለሰ Gashawe Meles

የቀንዲል መፅኤት አድራሻ / Kendil Magazine Address Wube Alemayehu Bergstr.6 97702 Münnerstadt E-mail [email protected] Website-kendilmagazine.wordpress.com Tel.(0152)12845925,102490

Kendil January ,2014 First Year No.4 2

Kendil January ,2014 First Year No.4 3

ማውጫ....... …......Content..........................!

የዝግጅት ክፍሉ መልዕክት......... Message to Our Readers.....1

ርዕሰ አንቀፅ.............Editorial...................5-6

ፖለቲካ...................Politics..................

ብዙ ያልተሄደበት የማንዴላ መንግድ................................................................. 7 በጀርመን ሙኒክ ለአባይ ግድብ የተዘጋጀው የቦንድ ሽያጭ

በተቃውሞ ተበተነ...........................................................................................10የወያኔ ጭቆና ይብቃን...........................................................................11

የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ በሳውዲ አረቢያ....................................................12

አይዘገይም ፍርዱ................................................................................13የሳውዲ አረቢያ አስፋልት በኢትዩጵያውያን ደም ጨቀየ.................................13

ከህወሓት የዘር ጭቆና ነጻ እንውጣ...........................................................14

ወገን ስቃይ በሳውዲ............................................................................14አቋማችንን እናስተካክል.................................................................15የኢትዮጵያውያን ስደት እንዴት ያብቃ?....................................................16

ወጣቶች በጋራ ለለውት እንነሳ..............................................................................17በጋራ በመታገል ሀገራዊ ግዴታችንን እንወጣ................................................17የጋራ ጠላታችን ህወሓት/ ኢህአዴግ ነው.....................18የኢትዮጵያ ሴቶች ወደ ትግል እንቀላቀል...........................................................18ምክር ለህወሓት/ ኢህአዴግ መከላከያ ሠራዊት............................................................19

ወያኔ በሴቶች ስም መነገዱን ያቁም...................................................................20የኢትዮጵያ ህዝብ በፃነት ለማስከበር በጋራ እንነሳ.........................................20የአንድነታች ጠላት የሆነውን ወያኔን ለመጣል እንታገል..................................21ለሀገራችን የመረጃ ነፃነት ትግል እናድርግ...................................................21ሰላማዊ ሰልፍ በባዕድ ሀገራት እና “አስራ አንደኛው ቀን” በሳውዲ አረቢያ ........22

Kendil January ,2014 First Year No.4 4

ርዕሰ አንቀፅ

የነፃነትና የይቅር ባይ ምልክቱ ኔልሰን ማንዴላ የአፓርታይድ ስርዓትን ለመታገል ከአምስት አስርትዓመታት በፊት ኢትዮጵያ ጭምር መጥተው የተለያዩ ወታደራዊ ስልጠናዎችን ወስደዋል።ማንዴላ ይህንን ረጅም ትግል ሲጀምሩ በህይወት ዘመናቸው የጥቁሮችና የነጮች የበላይነትን በመታገል ነፃናዲሞክራሲያዊት ሀገር የመመስረት ህልም ነበራቸው።ይህ የሚሳካ የማይመስል ህልማቸው ከ 27 ዓመታት የእስር ቤት ቆይታ በሃላ እውን ሆነ፡፡ማንዴላ በሰላማዊ ተቃውሞ የአፓርታይድ ስርዓትን በመገርሰስ እ.አ.አ በ 1994 የደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያዉ ጥቁር ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ።

ማንዴላ የአፓርታይድ ስርዐትን ገርስሰው አዲሲቱን ደቡብ አፍረካን የዲሞክራሲያው ስርዓት ካባሲያከናንቡ ያኔ የአፓርታይድ ስርዐትን ለመገርሰስ ከማንዴላ ጎን በመሆን የበኩሏል ጥረት ስታደርግ የነበረችው ሀገራችን ኢትዮጵያ ግን ከአፓርታይድ ስርዓት ወደማይተናነስ ወደ አዲስ የብሔር ፖለቲካ ስርዓት ገባች።ማንዴላ ለ 27 ዓመታት ታስረው በ 1994 እ.አ.አ የአፓርታይድ ስርዓትን ገርስሰው ወደ አዲስ ስርዐት ሲሸጋገሩ ሀገራችን ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ 1991 ወደ ብሔር ፖለቲካ አቀንቃኝነት ተሸጋገረች።እድለኛዋ ደቡብ አፍሪካ በዜጎቿ አጥንትና ደም ወደ አዲስ ስርዓት ስትሸጋገር እንደ አለመታደል ሆኖ በወቅቱ ዘረኝነትንና የአፓርታይድ ስርዐትን ለመገርሰስ በአፍሪካ አንድነት ድርጅት ጭምር ዋነኛ አቀንቃኝ የነበረችው ኢትዮጵያ እስከ አሁን ድረስ እየታገለችው ወዳለው ወደ ዘረኛውና የብሔር ፖለቲካ አቀንቃኙ ኢህአዴጋውያን ስርዐት ተዘጋገረች።

ይህ አዲሱ ብሔር ተኮር ስርዐት ሀገራችንን ወዳልተፈለገ መስመር እንድታመራ ያደርጋታል ብለው በአደባባይ የተናገሩና የተቹ ማንዴላ ያኔ ትግል ሲጀምሩ በነበረበት ወቅት ይሰጣቸው የነበረው "ሽብርተኛ "የሚለው ተቀፅላ ተሰጥቷቸው አሁን ድረስ በእስር ይማቅቃሉ።ወደ መፍትኤው ስንመጣ ማንዴለ ለዚህች ዓለም በርካታ ቁምነገሮችን አስተምረው አልፈዋል።ይቅር ባይነትና ጥንካሬን፣ትህግስትና ያለማቋረጥ ሙከራ ማድረግን፣ተስፋ አለመቁረጥንና ተባብሮ መስራትን ፣ሩቅ አላሚነትንና ህልመኛ መሆንን፣ መምራት መቅደም ብቻ ሳይሆን ሌሎችን ከፊት በማስቀደም መምራት ስንደሚቻልና ስልጣንን በፈቃደኝነት መልቀቅም አመራርነት እንደሆነና ሌሎች ቁም ነገሮችን አስተምረውንና አሳይተውን ያለፉት ማንዴላ አስተምዕሮዎቻቸው ከብዙዎቻችን ልብ አይጠፋም።እናም እኛ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ከማንዴላ አስተምዕሮዎች ልምድ በመውሰድ ሀገራችንን አሁን ካለችበት አስከፊው የዘረኛና የብሔር ፖለቲካ ስርዐት ለማላቀቅ የየበኩላችንን ጥረት ማድረግ ይኖርብናል።

Kendil January ,2014 First Year No.4 5

EditorialThe conflict between Mandel’s way and EPRDF ethnic politics!It was five decades ago that the icon of freedom and reconciliation Nelson Mandela acquired military training in Ethiopia. The intention of the training was to strengthen the military wing of ANC and uplift the struggle against apartheid system in South Africa. Mandela said he has devoted his life for Africans freedom and accordingly he started the long walk to freedom in the early 1940s. However in the early 1960s he was imprisoned by apartheid leaders and turned prisoner for three decades which is one third of his life span. After 27 years of imprisonment he could able to abolish apartheid system and win his dream, a dream in which all south Africans black and white live in a new free and democratic South Africa. In 1994 winning the election he become the first black south African President. However In 1990s when south Africa enter into a new system of politics where freedom and democracy are the rule of the game, our country Ethiopia earlier stating itself in the side of Mandel’s struggle against apartheid system, has been forced to accept a new system of politics where ethnic politics is the rule of the game. While Mandela struggle to abolish race and ethnic politics from Africa and from the world at large, our dictatorial leaders have been striving to implant ethnic based politics in the country. From the beginning up to now many politicians and scholars are critical of the ethnic based politics of EPRDF. However the ruling government which is comparatively similar with the apartheid system of ruling is branding the critics with a new name terrorist has been imprisoned many of the critics. we do not forgot that during the straggle against apartheid Mandela was labelled as terrorist by the apartheid regime. But we do have now the Mandela legacy that teach as reconsiliation and strangth, endurance and coopration, great dream and leadership. Therefore ,we Ethiopian should learn from the legacy of Mandela and struggle against the ethincist EPRDF Regime

Kendil January ,2014 First Year No.4 6

ብዙ ያልተሄደበት የማንዴላ መንግድ

By Wube Alemayehu ውቤ አለማየሁ Münnerstadt

የአፍሪከ የነፃነት ምልክትና የሚሊዮኖች ጀግና ኔልሰን ማነዴላ በመጨረኛ ለዕድሜ ተፈጥሯዊ ግዴታ እጃቸውን ሰጥተው በ 95 ዓመታቸው ለዘልዓለሙ አሸልበዋል። የቀድሞ የታይም መፅሔት ማኔጂንግ ኤዲተር ሪቻርድ ሰቴንግል ፤ማንዴላ "የነፃነት ረጅሙ ጉዞ" የተሰኘውን ግለ ታሪካቸውን ሲያዘጋጁ ከጎናቸው በመሆን አብሯቸውሰርቷል፤ በአንድ ወቅት ማንዴላን ሞትን በሚመለከት ጠይቋቸው "ሰዎች ይመጣሉ ሰዎች ይሄዳሉ።እኔም መጥቻለሁ ቀኔ ሲደርስ እኔም እሄዳለሁ" ብለውት ነበር።የወቅቱ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ ታህሳስ 5 እ.አ.አ ምሽት 8 ከ 50 አካባቢ በቴሌቪዥን ቀርበው የማንዴላን የህልፈት ዜና "ማዲባ ተለይቶናል" ሲሉ ለመላው ዓለም አሰሙ። ዓለማችን ተረት የሚመስ ነገር ግን በእውነት ታይቶና ተቀምሶ የተጣጣመ የነፃነት፣የህርቅና የይቅር ባይ ምልክቷን በሞት አጣች።ማንዴላ የመሞታቸው ዜና በተሰማ በአምስተኛው ቀን ታላቅ የመታሰቢያ ዝግጅት ተደረገላቸው።ማንዴላ እ.አ.አ ታህሳስ 15 ቀን 2013 ዓ.ም በተወለዱባት ኩኖ ለዘለአለሙ ተሰናበትናቸው።..... ነገር ግን ማንዴላ ማን ናቸው?ምን አይነት አስገራሚ ታሪኮችን አሳለፉ? በዚህ ወቅት ከአፓርታይድ ባልተናነሰ ስርዓት ውስጥ ለምንገኝ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን የማንዴላ አስተምዕሮ ምንድንነው? ከአፓርታይድ ስርዓት ገፅታዎች እጀምራለሁ፡

ደቡብ አፍሪካና የአፓርታይድ ስርዓት

የደቡብ አፍሪካ ታሪክ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ታሪክ በብዙ መልኩ የተለየ ነው። አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገሮች ከ 1880 ዎቹ እ.አ.አ ጀምሮ ነበር በቀኝ ግዛት ቁጥጥር ስር የወደቁት።ደቡብ አፍሪካ ግን በመጀመሪያ በደቾች ቀጥሎም በእንግሊዞች ቀኝ ግዛት ስር የወደቀችው ገና 1600 መጀመሪያ አንስቶ ነበር።ሁለተኛ ደቡብ አፍሪካ ከእንግሊዝ ቀኝ ግዛት ነፃ የወጣችው በ 1910 እ.አ.አ ሲሆን ሌሎች አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት ግን ከቀኝ ግዛት ነፃ መውጣት የቻሉት ከ 50 ዓመታት በሃላ ከ 1960 ዎቹ ጀምሮ ነው።ሦስተኛ ምንም እንኳን ደቡብ አፍሪካ በ 1910 እ.አ.አ ከቀኝ ግዛት ነፃ የወጣች ቢሆንም የአዲሲቷ ደቡብአፍሪካ መሪዎች ግን ሀገሬ ደቡብ አፍሪካውያን ሳይሆኑ ከአውሮፓ ለቀኝ ግዛት መጥተው ደቡብ አፍሪካ የተዋለዱ ነጭ አውሮፓውያን ነበሩ። አውሮፓውያን የደቡብ አፍሪካን ምድር ከመርገጣቸው አስቀድሞ የምድሪቱ ነዋሪዎች በአብዛኛው ኮሲሃንና ባንቱ በተባሉ ሀገሬ ነዋሪዎች ነበር የምትታወቀው።እኚህ ሀገሬ ደቡብ አፍሪካውያን ከ 1 ሺህ 5 መቶ ዓመታት በላይ በደቡብ አፍሪካ ምድር እንደኖሩ ይገመታል። እ.አ.አ በ 1910 ግን ደቡብ አፍሪካ ከእንግሊዝ ቀኝ ግዛት ነፃ ስትወጣ አፍሪካነር የተባሉት የደች ዘር ተወላጆች በአዲሲቱ የደቡብ አፍሪካ መንግስት የበላይነት ያዙ።ሀገሬ ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያንም መብቶቻቸውን መነጠቅ ጀመሩ።አፍሪካነርስ የተባሉት የአዲሲቱ ደቡብአፍሪካ ገዢዎች አዳዲስ ህጎችን ማውጣት ጀመሩ።አዳዲሶቹ ህጎች ቀለምን መሰረት ያደረገ የዘር ልዩነትን በግልፅ የሚፈጥሩና የሚደነግጉ ነበሩ።ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን የሚሰሩዋቸው ስራዎች ፣የሚማሩባቸው ትምህርት ቤቶች፣የሚኖሩባቸውን አካባቢዎች፣ግዥ የሚያከናውኑባቸው ገበያዎችና የመጓጓዣ አገልግሎቶችንም የሚለዩ ነበሩ። በአጭሩ አፍሪካነርስ በደቡብ አፍሪካ የአፓርታይድ ስርዓት እንዲወለድ ምክንያት ሆኑ።አፍሪካነርስ በፓርላማ ያላቸው መቀመጫ እየጨመረ ከመጣ ቱ ጋር በተያያዘ እ.አ.አ በ 1948 አፓርታይድ ብሔራዊ የደቡብ አፍሪካ መንግስት ፖሊሲ ሆኖ ተደነገገ።በአፓርታይድ ስርዓት ደቡብ አፍሪካ ነጮች፣ ኤስያን፣ የዘር ድብልቅ ያላቸውና በመጨረሻም ጥቁር አፍሪካውያን በሚል በአራት የዘርና የቀለም መለያዎች ተከፋፈለች። እንደየቅደም ተከተላቸውም ነጮች በስራ ፣ በትምህርት፣ በቤትና ጤናን በመሳሰሉት ጥቅማ ጥቅሞች የበላይ ተጠቃሚዎች ሆኑ። ኤስያና ድብልቅ ዘር ያላቸው ከነጮች ያነሰ ጥቅማ ጥቅም ቢኖራቸውም ከጥቁሮች ግን እጅግ የተሻለ ነበር።በመጨረሻም ጥቁር የሀገሬ ተወላጆች በማህበራዊና በመሰላሉ ጥቅማ ጥቅሞች ዝቅተኛው ደረጃ ላይ የሚገኙት ሆኑ። በአፓርታይድ ስርዓት እያንዳንዱ የደቡብ አፍሪካ ተወላጅ ጎሳዎች ነጮች ወደሚኖሩበት አካባቢ

Kendil January ,2014 First Year No.4 7

መድረስ አይፈቀድላቸውም።ይህ ተወላጅ ደቡብ አፍሪካውያን ይኖሩባቸው የነበሩት አካባቢዎች በአብዛኛው የተጎሳቆሉና ለኑሮ ምቹ ያልሆኑ እንዲሁም ምንም አይነት የማህበራዊ አግልገሎት ያልተሟላባቸው ነበሩ። በግብርናውም ቢሆን ምርታማ ያልሆኑ ናቸው።በአፓርታይድ ስርዓት ወቅት ተወላጅ ደቡብ አፍሪካውያን የፖለቲካ መብቶችም ያልተፈቀደላቸው ነበሩ። በስርዓቱ ተወላጅ ደቡብ አፍሪካውያን እንደ ዜጋ ካለመቆጠራቸው ጋር በተያያዘ የመምረጥና የመመረጥ መብትም አልነበራቸውም።ከእንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ነዋሪዎች ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱበትን ሁኔታ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ባለመቻሉ የፖሊስ ስራን ለማቅለል ሲባል ዘርና ቀለምን መሰረት አድርጎ የተከፈሉት አራቱን ነዋሪዎች የተለያዩ የመለያ ፓስፖርት እንዲኖራቸው ተደለገ።ያለ ፓስፖርቱ ወይም ፓስፖርቱ ከሚያዘው አካባቢ ውጭ ተንቀሳቅሶ የተገኑ በተለይ ተወላጅ ደቡብ አፍሪካውያን ለቅጣት ይዳረጉ ነበር።

አፓርታይድና አፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ

አፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ (ANC) በደቡብአፍሪካ የነጮች የበላይነትንና የአፓርታይድስርዓትን ለማስወገድ የተቋቋመ ድርጅትነው።ድርጅቱ በ 1912 ሲመሰረት ማንዲላ ገና የ6 ዓመት ጨቅላ ህፃን ነበሩ።ማንዴላ አፍሪካብሔራዊ ኮንግረስን በመቀላቀል በግልፅ ወደፖለቲካ ትግሉ የገቡት በ 26 ዓመታቸው ማለትምከተወለዱ ከሁለት አስርት ዓመታት በሃላ በ 1944 ዓ.ም ነበር።ማንዴላ በነበራቸው ከፍተኛየፖለቲካ እንቅስቃሴ እ.አ.አ ነሐሴ 5 ቀን 1964 በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ብዙምሳይቆዩ መንግስትን በሀይል ለመገልበጥ በሚልናበሌሎች ክሶች የዕድሜ ልክ እስራትተፈረደባቸው።.ውሳኔው ሲተላለፍባቸው ማንዴላእስከ ዛሬ በአስገራሚነቱ የሚታወሰውን ለ 4 ሰዓታት የረዘመ ንግግራቸውንአደረጉ።በንግግራቸው ማንዴላ"በህይወት ዘመኔራሴን ለአፍሪካ ህዝብ አሳልፌ ሰጥቻለሁ።በዘመኔየነጮችን የበላይነት እታገላለሁ። የጥቁሮችየበላይነትንም ጭምር እታገላለሁ።የኔ ገዢ ሀሳብናየምታገልለት መሰረታዊ አስተሳሰብ ሁሉም ሰዎችበደስታና በእኩልነት መኖር የሚችሉበትዴሞክራሲዊና ነፃ ማህበረሰብ መመስረት ነው። ማንዴላ ለረጅም ዓመታት በእስር የቆዩባት ክፍል

ይህ አመለካከቴ ምናባዊ ነው።በግልፅ ማሳወቅ ካስፈለገ ደግሞ ይህን ምናባዊ ሃሳቤን ለማሳካት ህይወቴን እስከመክፈል ድረስ ተዘጋጅቻለሁ" በሚል ህዝቡን አስደምመው ነበር። ከንግግሩ ነሃላ በፓርቲያቸው በተጀመረው ትግል ምክንያት ለ 27 ዓመታት ወደሚማቅቁባቸው እስር ቤቶችም ተወረወሩ።ለ 18 ዓመታት ሮቢን ደሴት ከዚያም ቀጣዮቹን ዓመታት ፖለስሞርና ቪክቶር ቬርስተር በተባሉ እስርቤቶች አሳለፉ።ማንዴላ የእድሚያቸውን አንድ ሦስተኛ በእስር ወደሚያሳለፉበት እስር ቤት ሲያመሩ የ 46 ዓመት ጎልማሳ ነበሩ።ማንዴላ እ.አ.አ የካቲት 11 በ 1990 ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከ 27 ዓመታት የእስር ቤት ቆይታ በሃላ ተለቀቁ።ማንዴላ ከእስር ሲፈቱ የ 72 ዓመት አዛውንት ነበሩ።ማንዴላ ቪክቶር ቬርስተር የተባለውን እስር ቤት ለቀው ሲወጡ በአንደበታቸው ለዓለማችን አንድ መልዕክት አስተላለፉ፤ እንዲህም አሉ " በአንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ። እርሱም የጥላቻና የበቀል በጥፎ ስሜቶቼን እዚህ እስር ቤት ጥያቸው ካልወጣሁ አሁንም እስር ቤት እንዳለሁ መሆኔን ነው" አሉ። በመቀጠልም ማንዴላና ሌሎች የፓርቲያቸው አመራሮች ያለፈው የአፓርታይድ ስርዓት ይቅር ወደሚባልበትና ወደማይደገምበት እንዲሁም መልሶ ወደማይታወስበት ምዕራፍ ሊያሸጋግራቸው የሚያስችላቸውን ውሳኔ በማስተላለፍ "የእውነት አፈላላጊና የእርቅ ኮሚቴ" አቋቋሙ ። በይቅርታና በዕርቅ ተመሰረተችው አዲሲቱ ደቡብ አፍሪካም በድጋሜ ተወለደች።ማንዴላም በ 1994 በደቡብአፍሪካ የተደረገውን ምርጫ በማሸነፍ በ 76 ዓመታቸው የደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚዳንት

Kendil January ,2014 First Year No.4 8

ሆነው ተመረጡ።

ማንዴላና ኢትዮጵያ

ማንዴላ በሰኔ 1961 ከፓርቲያቸውበተሰጠ መመሪያ መሰረት በተለያዩየአፍሪካ ሀገራት በመጓጓዝ ለፓርቲውየፖለቲካና የኢኮኖሚ ድጋፍ የማሰባሰብተልዕኮ ተሰጥቷቸው ነበር። ከሀገርመውጣት የማይፈቀድላቸው ማንዴላየተሰጣቸውን ተልዕኮ ለማሳካት "ዴቪድሞትሳማዪ "በሚል ስም ከሀገርመውጣት ቻሉ። ጥር 11 1962 መንዴላ በሚስጥርና በህገመንግድመንገድ ከሀገረ ደቡብ አፍሪካ ወጡ።ዓላማቸው ደግሞ የአፍሪካ ሀገራትመሪዎችን በማግኘት ለአፍሪካ ብሔራዊኮንግረስ የፖለቲካና የኢኮኖሚንጨምሮ የተለያዩ ድጋፎችንማሰባሰብና እርሳቸው አዲስላቋቋሙት የፓርቲያቸው ወታደራዊ ክንፍ ወታደራዊ ስልጠና ማውሰድነበር።ማንዴላ በዚህ ጉዞዋቸው በርካታ የአፍሪካ ሀገራትን የጎበኙ ሲሆን ዋነኛዋ ሀገር ደግሞ ኢትዮጵያ ነበረች።በ 1962 የመጀመሪያዎቹ ወራት ማንዴላ ጀነራል ታደሰ ብሩና ኔልሰን ማንዴላ

በአዲስ አበባ በሚደረገው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ስብሰባ ላይ መገኘት ችለው ነበር።ማንዴላ የኢትዮጵያን ምድር ከረገጡ በሃላ ወደ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የሚያደርጉት ጉዙ ቀላል እንዲሆንላቸው በንጉስ በሀይለስላሴ ትዕዛዝ "በዴቪድ ሞትሳማዪ" ስም ፓስፖርት ተሰጥቷቸው ነበር ። ከዚያም ማንዴላ የተሰጣቸውንተልዕኮ ለማሳካት ታንዛኒያ ፣ግብፅ፣ቱኒዚያ፣ሞሮኮ፣ጋና፣ሴኔጋልና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት መጓዝ ችለው ነበር።

ለማንዴላ ወታደራዊ ትምህርትና ስልጠና የሰጡት ኮሎኔል ፈቃዱ ወከኔ በጀነራል ታደሰ ብሩ ትህዛዝ ነበር ማንዴላን የማሰልጠን ስራ የጀመሩት። በወቅቱ ጀነራል ታደሰ ብሩ በ 1960 በንጉሱ ላይ የተደረገውን መፈንቅለመንግስት በማክሸፍ ከፍተኛ ሚና የተጫወቱ የፖሊስ ረዳት ኮሚሽነር ነበሩ። ኮሎኔል ፈቃዱ ወከኔ ደግሞ ከጀነራል ታደሰ ብሩ በታች በመሆን መሰረቱን ኮልፌ ያደረገው የልዩ ፖሊስ አድማ በታኝ ሀይል ባለስልጣን ነበሩ።ኮሎኔል ፈቃዱ ለኔልሰን ማንዴላ የተለያዩ የወታደራዊ ሳይንስና የተግባር ትምህርትና ስልጠናዎችን ሰጥተዋቸዋል። ከስልጠናዎቹ መካከል የሽምቅ ውጊያ ታክቲኮችና ሌሎች ስልጠናዎች ይገኙበታል።"ማንዴላ ጠንካራና ትጉህ ተማሪ ነበር።የተሰጡትን መመሪያዎች በአግባቡ የሚፈፅምና በጣም የሚወደድ ተማሪ ነበር" ብለዋል ኮሎኔል ፈቃዱ ስለ ተማሪያቸው ኔልሰን ማንዴላ በሰጡት አስተያየት።" እርሱን መውደድ ብቻ ሳይሆን ታፈቅረዋለህ" ሲሉ የተናገሩት ኮሎኔል ፈቃዱ ማንዴላን የማሰልጠን ሃላፊነት ይሰጣቸው እንጂ ከስልጠናው በመለስ ማንዴላ በወቅቱ የሰነቁት ዓላማ ምን እንደነበር የማያውቁና ሚስጥር ሆኖባቸው የቆየ እንደነበር ተናግረዋል።

ማንዴላ በወቅቱ የአፍረካን ነፃነትና አንድነት በሚያቀነቅኑት በኢትዮጵያ ንጉስ ቀዳማዊ ሀይለስላሴ ግብዣ ተደርጎላቸው ነበር የኢትዮጵያን ምድር ሊረግጡ የቻሉት ። ማንዴላ ለወታደራዊ ስልጠው ኢትዮጵያ በመጡበት ወቅት ኢትዮጵያ በአህጉሪቱ የግዙፍ ወታደራዊ ሀይል ባለቤት ነበረች። ወታደራዊ ሀይሉ በ 1960 ው የኮንጎ ቀውስ የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ሀይል አካል ከመሆኑም በተጨማሪ ከዚያአስር ዓመታት ቀደም ብሎ የኢትዮጵያ ወታደሮች በኮሪያው ጦርነት ላይ ተሳታፊዎችም ነበሩ።

Kendil January ,2014 First Year No.4 9

አፄ ሀይለ ሥላሴ ለኔልሰን ማንዴላ እንዲሰጣቸው ያደረጉት ፓስፖርት

ከዚህ በተጨማሪም ንጉስ ሀይለ ሥላሴ ለአፍሪካ ነፃነት የሚታገሉ በርካታ የነፃነት ታጋዮችን ኢትዮጵያ ድረስ በመጋበዝ በምድሪቱ ወታደራዊ ስልጠና እንዲያገኙ አድርገዋል። ማንዴላም እንግዲህ በወቅቱ የዚህ አንዱ አካል መሆናቸው ነው።ማንዴላ በኢትዮጵያ የነበራቸው ቆይታ እጅግ በጣም አስደሳችና በወቅቱ ስልጠናውን ይወስዱበት የነበረው አካባቢ ከገጠራማው የደቡብ አፍሪካ የኑሮ ሁኔታ ጋር ይመሳሰል እንደነበር "የነፃነት ረጅሙ ጉዞ " Long Walk To Freedom በተሰኘው የግል ታሪካቸው ላይ አስፍረውታል። ወደ ገፅ 24

በጀርመን ሙኒክ ለአባይ ግድብ የተዘጋጀው የቦንድ ሽያጭ በኢትዮጵያውያን ተቃውሞሳይሳካ ቀረ! በአበራ ሽፈራው /ከጀርመን/

የህወሃት/ኢህአዴግ ቡድን በጀርመን አገር ሙኒክ ከተማ በ 02-11-2013 ባዘጋጀው የአባይ ግድብየገንዘብ ማሰባሰብ ፕሮግራም ላይ ከጀርመን ልዩ ልዩ ከተሞች የተሰባሰቡ የልዩ ልዩ ፓርቲዎች አባላትናደጋፊዎች እንዲሁም የህወሓት ብዝበዛ ያንገሸገሻቸው አገር ወዳድ ኢትዮያውያን በቦታው ቀድመውበመገኘትና ተቃውሞአቸውን በማሰማት የበዝባዦች ዓላማ እንዳይሳካ አድርገዋል። ብዛት ያለው ሰው የህወሃትየበዝባዥ ቡድን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ በመግባት፤ አዳራሹን በመቆጣጠር፤ በኢትዮጵያ ውስጥ የህወሃትቡድን እየፈጸመ ያለውን ግፍና ሰቆቃ ሳይገደብ አባይን መገደብ ተገቢ አለመሆኑን የሚገልጹ ልዩ ልዩመፈክሮችንና ኢትዮጵያዊ ዜማዎችን በማሰማት አዳራሹን በተቃውሞ ተቆጣጥረውት አምሽተዋል።የአባይ መገደብ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ፍላጎት መሆኑን የገለጹት ተቃዋሚዎቹ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚከናወነውግፍ ማለትም የሰባዓዊ መብት ጥሰት፣ የንግድ ብዝበዛ፣ በማንኛውም መልኩ በኢትዮጵያ ያለው የህወሃት

Kendil January ,2014 First Year No.4 10

ፍጹም የበላይነት እንዲያበቃ ህወሃትን መታገሉ አስፈላጊነቱን ኣጽንኦ ሰተውበት ተነጋግረውበታል።በዝግጅቱ መታወክ ምክንያት የፕሮግራሙአዘጋጆች በመደናገጥ ፖሊሶችንበመጥራታቸው ፖሊሶች በከፍተኛ ቁጥርበስፍራው የደረሱ ሲሆን ከተቃዋሚዎቹመካከል ለፖሊሶቹ ተወካዮች ጉዳዩንበማስረዳት የፖሊሶቹ ተወካይ በኢትዮጵያውስጥ ያለውን ጭቆናና ግፍ ከተቃዋሚዎቹአንደበት የተረዱት ሲሆን ፖሊሶቹምጉዳዩን በማግባባት የተወሰነ ጊዜ ሰጥተውተቃዋሚዎቹ ጉዳያቸውን ለተወሰነ ጊዜአከናውነው እንዲጨርሱ ካደረጉ በኃላተቋውሞው በህወሃት በዝባዦች ውርደትተጠናቋል።

በዚህ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ላይ የተገኙትኢትዮጵያውያን ለማየት እንደሞከሩትናእንደተረዱት ከሆነ ብዙዎቹ ስብሰባውንያዘጋጁት ሰዎች ከአንድ አካባቢየተሰባሰቡና ኢትዮጵያን የሚወክሉባለመሆናቸው ዛሬ ኢትዮጵያ በጥቂትየህወሓት በዝባዦች እጅ መውደቋንናበግልጽ የታየበት በመሆኑ እጅግ ያዘኑ ሲሆን ከዚህም በላይ ደግም በኢትዮጵያውያን ስም ከዓለም ከተበተኑኢትዮጵያውያን ለቁጥጥር በማያመች መልኩ ገንዘብ እየሰበሰቡ የጥቂቶችን ኪስ ለማደለብ ልዩልዩፕሮጀክቶችን እየነደፉ እንደሚንቀሳቀሱ በቀላሉ ለመረዳት ብዙዎች እድልን ያገኙበት ሰዓት ነበር::በአዳራሹ ውስጥ ከፍተኛ የምግብና የመጠጥ ድግስም ተዘጋጅቶ የነበረ ሲሆን ውስኪን ጨምሮ ልዩልዩመጠጦችና ምግቦች በአዳራሹ ውስጥ ታይቷል:: ይሁንና የፕሮግራሙ አዘጋጆች ይህንን ያሰቡትን ጭፈራእንዳቀዱት ሳይሆን ባልታሰበ መልኩ ፕሮግራማቸውን ለማጠናቀቅ ተገደዋል:: ከዚህም ለመረዳትእንደተቻለው ህወሃቶች ከዚህ በሗላ በተለይምበአውሮፓ አገራት እንደፈለጋቸው በኢትዮጵያውያንስም ሊነግዱ እንደማይችሉ ትልቅ ምልክት መሆኑንብዙዎች ተስማምተውበታል:: ይህንን ተቃውሞበልዩ ልዩ የኢትዮጵያውያን ውብሳይቶችና ኢሳትንጨምሮ ዘግበውታል::

የወያኔ ጭቆና ይብቃንTedela GetenetOberer Manikai 3

እነሆ እኛ ኢትዮጵያውያን በወያኔ ግዞት ከወደቅን22 አመታት ተቆጠረ። በእነዚህ ዓመታት የኢትዮጵያህዝብ ያልሆነው ነገር የለም። አማራውን የቀድሞውዘመን ናፋቂ ወይም ነፍጠኛ ኦሮሞውን አሸባሪ ይላል።ለነገሩ በወያኔ ዘመን ያልተሰጠን አዲስ ስም የለም።ይሁንና በሀገራችን ውስጥ ከወያኔ የበለጠ አሸባሪአልተፈጠረም። ለምን ቢባል ፈንጅ የሚያፈነዳውእራሱ፤የሚታሰሩ ግን የአማራ ወይም የኦሮሞ ልጆች ናቸው። ከዚህም አልፎ የብዙ ብሔር ብሔረሰቦችመኖሪያ የሆነችውን ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር እዳትኖር የሚፈልግ የ 21 አመት የሀገር ቀንደኛ ጠላት የዘመኑእንክርዳድ ወያኒ ብቻ ነው።ወገን ወያኔ በኢትዮጵያ ላይ እያደረሰ ያለው ግፍና መከራ ሊቆም ይገባዋል። ይህንን

Kendil January ,2014 First Year No.4 11

አስከፊ ጭቆና ከዚህ በላይ የምንሸክምበት ጫንቃ ወይም ጀርባ የለንም። የእኛ ዝምታ ለወያኔ እፎይታእየሆነለት ነው ።ስለዚህ የወያኔን ጭቆና ሊቆምና በቃህ ልንለው ይገባል። ጊዜውም አሁን ነው። ዜጋው በአረብእጅ በአደባባይ ሲታረድ፣ አንዲት ሴት በህብረት ስትደፈር የማይሰማው ፣በሀገሯ ኤምባሲ ደጃፍ ስትገደል ተውየማይል፣ ከዚህም አልፎ በሀገር ቤት ያሉ ኢትዮጵያውያን ተዋረድን ድምጻችንን በሳውዲ ኤምባሲ በር ላይሰላማዊ ተቃውሞችንን እናሰማ በማለት የወጡትን ሰላማዊ ዜጎች ከሳውዲ አረቢያ ፖሊሶች ባልተናነሰ ሁኔታበዱላ የሚደበድብን መንግስት ብለን ልንጠራው አይገባም። አሸባሪ የሳውዲ ቅጥረኛ እንጂ ሊላ ምን ልንለውነው? እንዲህ ያለ አስከፊ ስርዓት ኢትዮጵያ በታሪኳ ገጥሟት አያውቅም ! ዝም ካልነው ያለንን ታሪክ ሙሉለሙሉያጠፋዋልና አንድ ሁነን ልንታገለው፣ ልናስወግደውና ጭቆናው በቃን ልንለው

ይገባል!

የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ በሳውዲ አረቢያBy Samuel Menase በሳሙኤልምናሴ

Homburgሳውዲ አረቢያ 27 ሚሊዮን የሚጠጋ የህዝብቁጥር አላት። ከዚህ ወስጥ 9 ሚሊዮኑ በተለያዩየስራ መስኮች የተሰማሩ የውጭ ሀገር ዜጎችናቸው።በአሁኑ ወቅት ሳውዲ አረቢያከአጠቃላይ ህዝቧ 12 በመቶው የሚተጋውስራ አጥ ነው።በዚህም የተነሳ ሀገሪቱ ከፍተኛቁጥር ያላቸው በተለይ ኢትዮጵያውያንን ከሀገሯእያስወጣች ትገኘለች።ዜጎቻችን ከሳውዲአረቢያ ስቃይና መከራ ሰቆቃና የመብትጥሰቶች በተሞላበት መንገድ ነው።

በኢትዮጵያ በዓመት በአስር ሺዎች የሚቂጠሩወጣት ልጃገረዶች መንገዳቸውን ወደመካከለኛው ምስራቅ ያደርጋሉ።ልጃገረዶቹ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት በቤት ሰራተኝነት፣በህፃናትተንከባካቢነት፣በፅዳት ሰራተኝነትና በሌሎች የስራ መስኮች ለመሰማራት ነው የኤደን ባህረ ሰላጤንየሚያቋርጡት።

የኢትዮጵያ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደሚገልፀው በ 2012 እ.አ.አ ብቻ 2 መቶ ሺህየሚሆኑ ሴቶች በአብዛኛው ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ተጉዘዋል ።አምነስቲ ኢንተርናስናልን ጨምሮአብዛኞቹ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ድርጅቶችና አለምአቀፉ የሰራተኞች ድርጅት በአረብ ሀገራት

በሰራትኝነት የሚሄዱ ልጃገረዶችና ወጣት ወንዶች ለተለያዩ አካላዊ ጥቃቶች፣ጤናማ ላልሆኑ የስራ ሁኔታዎችናለተለያዩ መገለልና መድሎዎች የተጋለጡ እንደሆኑ ይገልፃሉ።ተመላሽ ኢትዮጵያኑም ስለሳዉዲ አረቢያቆይታቸው ተመሳሳይ በሆነ መልኩ አንድ የሚናገሩት እውነታ አለ።

ተመላሾቹ የሳውዲ አረቢያ ደህንነቶችና ወጣቶች የተለያዩ የመብት ጥሰቶችን እንዳካሄዱባቸውና አጠቃላይየሳውዲ አረቢያ ህዝብም ቢሆን ለውጭ ሀገር ዜጎች የጥላቻ አመለካከት እንዳላቸው።የኢትዮጵያ መንግስትእንደገለፀው እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ 120 ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

Kendil January ,2014 First Year No.4 12

አይዘገይም ፍርዱ

By: Alem kebede Weldy

Münnerstadt

ኢትዮጵያዊ ወገኔ ሀገር አልባ ሆኖ ብሶቱ ፀንቶበት

አንዱ ሲባል ሌላው ፆም ማደሩ ከፍቶት ይሻላል በማለት ኑሮን ለመለወጥ ተርፎ ለማይደላ

ወገኑን እራሱን እረዳለሁ ብሎ ሳይበላ ተበላ ኢትዮጵያዊ ወገኔ በነታሀኩና ባለውለታው

እንኳንስ ለሰው ዘር ለእንስሳው የሚያዝነው የአረብ የሰው ጅብ ዘነጣጥሎ በላው አንጀት በሚበላው ዋይታና ስቅስቅታ በጨካኞች ስለት ህልማቸው ተመታ

ቃርሚያም እህል ሆኖ አረብ ጠገበብን ቀን ጥሎን እደጁ አግኝቶ ገደለን

እኛ አቅም የለንም ወዳምላክ ጮሕናል ቃል ብቻ ተናገር አንዳችም ሰይዘገይ ህዝብህ ፍርድ ያገኛል።

የሳውዲ አረቢያ አስፋልት በኢትዩጵያውያን ደም ጨቀየ

ሀና ደምስSchlossbers 1

የሳውዲ መንግስት አሁን እየደረገ ያለውድርጊት ለሀገራችን ኢትዮጵያ ብሒራዊውርደት ነው እኛ በቀኚ ገዝወች ያልተደፈርን ማለት ለነጭ ያልገበርን ያልተገዛን ነን የሚለውሪኮርድ በወያኒ አጋፋሪነት በሳውዲአረቢያፖሊስ አካይነት ሊሰበር ችሎል ከዚህ በኃላየጥቁር ተምሳሊት የሚለው ፉከራ ሽለላቀረርቶ የአደዋድል የነጻነት ቀን የሚከበርበትቀን ተስርዞ ጥቅምት 24 በየአመቱየኢትዩጵያዊያን የውርደት ቀን ተብሎ ማክበርሊገባን እንደሆነ ወያኒ አመቻችቶየ 2006 ዓ.ም የውርደት ገጸበረከት አቅርቦ

አንገታችንን አስደፍቶናል።ኢትዮጵያዊ ወገኒይህንን ውርደት እንደማንቀበለው ልናሳውቀውይገባል ወያኒወችን እናንተ ኢትዮጵያውን አይደላችሁም፡ወገኖቻችን ሲታረዱ የማይሰማው ቅጥረኛ ዘረኛ ሙሰኛለአረብ በባርነት አሳልፎ የሸጠንን የወንበዲ ቡድን ማስወግድ አለብን በአረብ አስፋልት የሀገሩን ባንዲራአድርጎ በጠላት ሀገር የተሰዋው ጀግና ታሪክ የማይረሳው ኢትዮጵያዊው ነው።በሀገሩን ባንዲራ መገነዝ መቀበርማንም የማያገኘው እድል ይህ አሳፋሪ አዋራጅ ቡድን ሲለቅ ታሪክ ይዘግበዋል።በአረብ አረመኒወች የፈሰሰውየወገኖቻችን ንጹህ ደም ፈሶ አይቀርም ብድር በምድር እንደተባለው በአረበ የተደፈራችሁ።የተገደላችሁየተሰቃያችሁ ወገኖቺ ደማችሁ ፈሶ አየቀርም በቁርጥ ቀን ልጆቻችሁ እጥፍ ድርብ ሆኖ ይመለሳል እላለሁ

Kendil January ,2014 First Year No.4 13

በሳውዲአረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየተደረገ ያለውን ግፍ በመቃወም በጀርመን ኑረንበርግ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ።ሚሚ ኃብተማርያምከጀርመንበኢሕአፓ ደጋፊ ኮሚቴና የኢህአፓ ወክንድ ተቀናጅተው በዛሬው ዕለት በ 23/11/2013 በጀርመናዊቷ ኑርንበርግ ከተማ የኢሕአፓ ደጋፊ ኮሚቴና ወክንድ አባላት፣ በሌሎች የኢትዮጵያ ተቀዋሚ ፓርቲ አባላትና አመራሮች እንዲሁም የኢትዮጵያ ደጋፊዎች ጭምር የተሳተፉበት የተቃውሞ ሰልፍ በከተማዋ ልዩልዩ ስፍራዎችተደርጓል። የሰልፉም ዓላማ በተቃውሞ ሰልፉ ላይ እንደተገለጸው ከሆነ በሳውዲአረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየተደረገ ያለውን ግድያ ፣እስራት፣ ሴቶችን አስገድዶ መድፈርና ሌሎች ኢ-ሠብአዊ ድርጊቶችና ግፍች በመቃወምና፣ ለዚህም አገራዊ ውርደት መነሻው የህወሃት/ኢህአዲግ መንግስት መሆኑን በማመን የኢትዮጵያዊውንም ሥርዓት በመቃወምም ታላቅ የሆነ ተቃውሞም በኢትዮጵያው መንግስት ላይ ሰንዝረዋል። በሰልፉ ላይ ከተደመጡት መፈክሮች መካከል · ሳውዲአረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የምታደርገውን ግድያ፣ እስራት፣ አስገድዶ መድፈር አቁሚ።· የኢትዮጵያ መንግስት ለጥቃቱ ተባባሪ በመሆኑ አዝነናል።· ጀርመን ለኢትዮጵያው አንባገነን ሥርዓት መርዳትን አቁሚ።· ብሔራዊ ውርደት ይብቃ! እናሌሎችም ይገኙበታል።በመጨረሻም የተለያዩ ሰዎችና የፕሮግራሙ አዘጋጆች የማጠቃለያ ንግግር ካደረጉ በኋላ ሰልፉ ተጠናቋል።

ከህወሓት የዘር ጭቆና ነጻ እንውጣ

ByLidiaMebrate/ሊዲያመብራቴGermany,Coburg/ጀርመን ኮቡርግ/

በዓለማችን ተሰምቶ ባልታወቀ መልኩ ይበልጡንም አሁን ባለንበት ዘመን አገራት በዲሞክራሲያዊ ምርጫአምነው የህዝብ የበላይነት በነገሰበት ዘመን ዛሬ ኢትዮጵያ በህወሓት የዘር ግንድ የበላይነት ለከፍተኛየአፓርታይድ ሥርዓት ሥር ወድቃለች::በዚሁ ጉዳይ ላይ ሠፊ ትንተና መስጠት አያስፈልገኝም ማንምኢትዮጵያዊ ሁሉ አገሪቷ በህወሃቶች እጅ መውደቋንና የህወሓት የዘር ጭቆናም ከመቼውም ግዜ መባባሉንከማንም የተሰወረ ሃቅ ነው::ዛሬ ኢትዮጵያውያን በኢኮኖሚና የፖለቲካ መድሎ ውስጥ ወድቀን እንገኛለን ከዚህም በላይ መራርየሚያደርገው የአገሪቷ ሃብትና ንብረት፣ መሬትና የተፈጥሮ ሃብቶች በሙሉ በጥቂት የወያኔ ኋይሎች እጅለመወደቁ ከማንም ኢትዮጵያዊ የተሰወረ አይደለም :: የፖለቲካ ተሳትፎ በህወሃቶች በመድሎ መፈቀዱ፣የአገሪቷ ወታደራዊ ኃይል በሙሉ በህወሃቶች እጅ መውደቁ፣ የትምህርት እድልና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞችበሙሉ በህወሃቶች በሚጠቅም መልኩ በግልጽና በስውር እየተፈጸሙ መሆናቸው በግልጽ ይታያል::እንግዲህከህወሓት የዘር ጭቆና ለመውጣት ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ ህወሓትን በአገርና በህዝብ ጠላትነትበመፈረጅ በግልጽ መታገል ይኖርበታል:: ስለሆነም ከህወሓት የዘር ጭቆና እራሳችንን ማላቀቅ ያለብን መሆኑን አምነን እራሳችን ለትግል ካላነሳሳንበደቡብ አፍሪካ ከታየው የአፓርታይድ አገዛዝ በላይ የኢትዮጵያዊው የህወሓት ሥርዓት እጅግ በአስከፊ ሁኔታላይ እየጣለን መሆኑን ልንገነዘብ ይገባናልና ህወሓት ለመጣል እንነሳ::ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

የወገን ስቃይ በሳውዲBy Hana Meshesha ሃና መሸሻ Bayreuth

በሳውዲ በወገኖቻችን ላይ እየተደረገ ያለው ኢሰብአዊ ድርጊት የሚሰቀጥጥና እጅግ ሚያሳዝን ነው።አሁን ባለንበት በ 21 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ይፈጠራል ተብሎ በማይታሰብ ሁኔታ እኛ ኢትዮጵያውያን ብሔራዊ ውርደትን የተዋረድንበት ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም።ሰብአዊ መብቶች ሀገር፣ድንበር፣ዜግነት ወይም ሌላ መለኪያዎችን ሰይለዩ መብቶቹን ሰው በመሆናቸው ብቻ ሊያገኙት የሚገባ ክብር ነው። ያም ሆኖ በዚህ በዘመናዊው ዓለም እንስሳት እንኳን ያገኙትን ክብር

Kendil January ,2014 First Year No.4 14

ኢትዮጵያውያን ተነፍገው በርያድ ስደተኛ ወገኖቻችን እንደ በግ በአደባባይ ሲታረዱና በጭካኔ ሲደበደቡ፣ህፃናት በርሃብና በእርዛት ሲቀጡ፣ሴቶች እህቶቻችን በአሰቃቂ ሁኔታ ሲደፈሩ ፣ይህን ሰቆቃ ማየቱና ማዳመጡ ምን ያህል ያሳምማል!ለዚህ ሁሉ ግፍና ስቃይ ተጠያቂው ማን ሊሆን ይችላል? በችግር ላይ የወደቁትን ወገኖቻችንን በምንችለው አቅም እየረዳን የችግሮቻችን ምንጭ ሆነው ወያኔ ላይ የተባበረ ክንዳችንን እናንሳ!

አቋማችንን እናስተካክል

By Naomi Tesfaye ናሆሚ ተስፋዬ

Nürnbergዛሬ እኛ ኢትዮጵያውያን የተቸገርንበት ትልቁ ነገርቢኖር በዓላማችንና በአቋማችን መፅናትአለመቻላችን ነው።ማንም እንደፈለገ እየተነሳሀገራችንንና ህዝባችንን የሚሰድቧትና የሚንቋትየአንድነታችንና እርስ በእርስ ያለመግባባታችንችግር ነው።

እንደሚታወቀው እኛ ኢትዮጵአውያን የሰውንየማንነካና የራሳችንን የማናስደፍር ኩሩና ጀግናህዝብ ነን።ዛሬ ዛሬ ግን ኢትዮጵያውያን መታወቂያችን ሌላሆኗል።የዓለማችን ሀገራት እያደጉና እየበለፀጉበመጡበት በአሁኑ ወቅት ለዚህ ያልታደለችውሀገራችን ብቻና ብቻ ናት።

ለዚህ ሁሉ ተጠያቂ እኛው ራሳችን ዜጎቿ ነን።ይህምንም ጥያቄ የለውም።የመጣብንን አሜን ብለንከነችግራችን በፀጋ መቀበላችን ለብዙ ችግርናመከራ አጋልጦናል።

ይህ በዚሁ ከቀጠለ ወደ አሳዛኝና ሰፊ ችግር ውስጥ እንደምንገባ ምንም ጥርጥር የለውም። ለሁሉም መፍትኤውያለው በእጃችን ነው።ሀገራችንንና

ዜጎቻችንን ነፃ ማውጣት ያለብን እራሳችን ነን።ከሩብ ምዕተ ዓመታት ላላነሰ ዘመን ሀገራችንን ወደማትወጣበትአረንቋ የከተታት የወያኔ አገዛዝ በማላቀቅ ሀገራችን ወደተሻለ ደረጃ እንድትደርስ ሁላችንም የቻልነውን ያክልመታገል አለብን።

ያንን ሳናደርግ ሁሉን ነገር በቸልተኝነት የምንመለከት ከሆነ የዓለም መሳቂያና መሳለቂያ እንደምንሆንአልጠራጠርም።

ለዚህም ማሳያ ዛሬ በሳውዲ አረቢያ በወንድምና እህቶቻችን ላይ እየደረሰባቸው ያለው ግፍ ትልቅ ማሳያ ነው።

ዜጎቻችን በሀገር ውስጥም ይሁን በውጭ እየደረሰብን ያለውን በደል ከዚህ በተሻለ መንገድ መቃወምይኖርብናል፡፤ሀገራችን የሁላችን እንደመሆኗ መጠን ሁላችንም በጋራ መታገል ይኖርብናል።

Kendil January ,2014 First Year No.4 15

የኢትዮጵያውያን ስደት እንዴት ያብቃ?

በአቤል ንጉሴ ፍቃዱ

ከጀርመንየኃይለሥላሴ መንግስት ባከተመበትና የደርግመንግስት በተተካበት ወቅጥ የተማሩኢትዮጵያውያን ይዘዋቸው የተነሱት የወቅቱየፖለቲካ አስተሳሰቦችና ሥልጣንን ለመያዝየተደረጉት ትግሎች ብዙዎችን በነጭ ሽብርናበኃላም በቀይ ሽብር አቀንቃኞች መካከል የደምመፋሰስ በተደረገበት ወቅት ወታደራዊው ደርግየታጠቀ ኃይል ስለነበረና ሌሎች ኃይሎችንለመቆጣጥር ሰፊ የደም ማፍሰስ ተግባርበመፈጸሙ ጋር ተያይዞ ብዙዎች እራሳቸውንለማዳን ወደተለያዩ ጎረቤት አገራትና በኋላምወደአሜሪካና አውሮፓ አገራት ለመሸሽቢገደዱም እንደዛሬው የህወሃት /ኢህአዴግዘመን ግን ኢትዮጵያውያን ለሰፊ ስደትተዳርገን የምንገኝበት ዘመን እንደሌለ እሙንነው::

በአሁኗ ኢትዮጵያ ፍጹም ጭቆናና ጥቃት በኢትዮጵያውያን ላይ በገዥው መደብ በተከታታይ መፈጸሙና የሰብዓዊ መብት ረገጣው በህወሃት ዘመን ከመቼውም በላይ ወሰን በሌለው መልኩ መከናዎኑብዙዎችን ለከፍተኛ ፍልሰት ዳርጎናል:: ይህ የዘመናችን ገዢ መደብ በማሰር፣ በመግደልና በማሳደድ ብቻየተገታ ስርዓት አይደለም:: ይልቁንም የሰብዓዊ መብት እረገጣው እንዳለ ሆኖ ሌሎች የማህበራዊና የፖለቲካእንዲሁም የኢኮኖሚ ጥቅሞችንም በሙሉ ተቆጣጥረው ሰዎች እንዚህን መብቶቻቸውን ለማስከበርተፈጥሮአዊና የአገሪቷን የተጻፉ ግን በተግባር የማይታዩ ህጎችን ተጠቅመው መብቶቻቸን ለማስከበር በሚነሱናመብቶቻቸውን ለማስከበር በተሰባሰቡ ቁጥር በገዢው መደብ በጥሩ ያለመታየታቸው ይልቁንም ለተለያዩሰብዓዊ፣ ማህበራውና ኢኮኖሚያዊ ጥቃቶች እንድንጋለጥ መደረጉ ከማንም ኢትዮጵያዊያን የተሰወረአይደለም:: ለምን ህወሃት ይህንን ያደርጋል? ለምን የህዝቡን መብት በዚህ መልኩ ይጨፈልቃል ?የሚለውን ለመመለስ ከፈለግን ትልቁ ነገር ህወሃት በአደባባይ እያደረገ ያለውን ብቻ በመመልከት መመለስይቻላል::ይህም ህወሃት ከጅምሩ ዲሞክራሲያዊና የህዝቦችን ነጻነት ለመጠበቅ የተነሳ ድርጅት ሳይሆን ጥቂቶችምን አልባትም በህወሃት ዙሪያ የተሰባሰቡ ጥቂት ሃይሎች በወቅቱ የነበሩትን አስተሳሰቦች ፖለቲካዊ ይዘትኖሯቸው ብንታገልና ብንችል ትግራይን ከተቻለም ደግም ኢትዮጵያን በመቆጣጠር በቡድኖቹ ዙሪያ የታሰበውን የኢኮኖሚ የበላይነትን ጥማትለማርካት፣ ለማስፈንና ለመበዝበዝ ያስችላቸው ዘንድ በአንደበት ብቻ የማይፈጽሙትን ዲሞክራሲና ፍትህንሽፋን አድርገው የህዝቦችን የነጻነትን ጥማትና የደምን ዋጋ በቁጥጥር ስር በማድረግ ዛሬ ህወሃቶች ፍጹምወደሆነ የኢኮኖሚና የፖለቲካ የበላይነትን ለማንገስ ይዘውት የተነሱትን ስውር ዓላማ ግቡን እንዲመታ አደረጉትይህም ለኢትዮጵያዊያን የዘር ጭቆናን ይልቁንም አመጣ::ይህም አጠቃልይ ወታደራዊኃይሉን፣ኢኮኖሚውን፣ንግዱን፣የአገሪቷ የመሬትና ሌሎች ተፈጥሮአዊ ሃብቶችን፣ አጠቃላይ የፖለቲካሥልጣን፣ የፖሊስና የጉሙሩክ እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚንስቲር መስሪያ ቤቶች በሙሉ በቁጥጥር ስርወደቁ::

እንግዲህ ህዝቡ እነዚህን እውነታዎች በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ለመቃወም የተነሳውን ሁሉ ማሳደድ፣

Kendil January ,2014 First Year No.4 16

ማሰር፣መግደል፣ማፈናቀል፣ማጥፋት፣ ንብረትን መውረስ፣ንግድን ለኪሳራ መዳረግና ከንግድ ውጭ ማድረግ፣ልዩልዩ መብቶችን ማለትም የሥራ እድልን፣የትምህርትንና የሥራ ዕድገት መብቶችን መንጠቅና ሌሎችንምበማድረግ የህዝቡን የፖለቲካ፣የማህበራዊና የኢኮኖሚ መብቶችንም በመግፈፍ ከሰባዊነት ውጭ እንዲሆንበማድረግ ህወሃት በተጠና መልኩ እየተገበረ ያለው አካሄድ መሆኑን ያልተረዱ ይኖራሉ ለማለት እቸገራለሁ::እነዚህን ሁኔታዎች ለማስፈጸም ይረዳው ዘንድ ህወሃት የዘረጋው መዋቅርንም ብንመለከት ይኸንኑ ያሳየናል::

እንግዲህ ህወሃት እንዚህ ጥቅሞቹን ለማስጠበቅ ሲል በሰብዓዊ ኢትዮጵያውያን ላይ እየወሰደ ያለው ጭካኔህዝቡን ለስደት ዳርጎታል:: እነዚህን ሁኔታዎች ለመቀየር ኢትዮጵያውያን ከመቼውም ጊዜ በላይ በመነሳትየአገሪቷ ንብረቶች፣ የመኖር ተፈጥሮአዊና የአገሪቷ ህግጋት እንዲከበሩ ማድረግና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሁሉየአገሪቷ መብት ተጠቃሚ መሆን እንዳለበት አምኖ ህዝቡ የበላይ ሆኖ የሚኖርባት ኢትዮጵያን በመፍጠርየተሰደደውም ከስደት ሊድን የምንችልበትንና ሌሎችም ከዚህ በኋላ ከአገር እንዳይሰደዱ የሚያደርግ ሁኔታለመፍጠር ቆርጦ መታገል ይኖርብናል:: ይህ ደግሞ መስዋዕትነትን የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊሁሉ ዋጋ ሊከፍልና የኢትዮጵያውንን ስደት ልናስቆም የሚገባን እኛው ነን:: ህወሃት ቢቻል ማሳደድ ካልሆነምእንድንሰደድ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ካልሆነም አስገድዶ ማሰደድን በበቂ ሁኔታ ተክኖበታልና ይህንንየምናስቆምበትን ሁኔታ መፍጠር ይኖርብናል:: እኛም ይህንን ሊያስቀሩ የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ለማፋጠንመነሳት ያለብን ጊዜው አሁን ነው:: ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይባርካት!

ወጣቶች በጋራ ለለውት እንነሳ

By Binyam Haile ቢንያም ሀይሌNürnbergወታቶች ራሳቸውን ለመለወት ከበፊቱ በተሻለ ጥረት ማድረግ አለባቸው።የአፍዝ አደንግዝ ሱስ፣የአልኮል መጠጦች ሱሰናና ሰካራም መሆንና የተለያዩ ፈር አሳች ነገሮች ሰለባ መሆን ወታቱ በሀገሩና በወገኑ ላይ እንዳአተኩርና ሀገራዊ ቅርሶችንና ፀጋዎች የሆኑትን እምነቶችና እአሳሱትና እያዳከሙት በቀላሉ የሚረታና የሚሰነፍ እያደረጉት ነው።ነፃነትና ብሔራዊ ሉአላዊነት በዜጎች ትግልና መስዋዕትነት ነው ተጠብቀው የሚኖሩት።ይህንን መስዋዕትነት ለመክፈል የተዘጋጀ በሌለበት ዌኢም ባነሰበት ወቅት ነፃነትና ሉዓላዊነት እንዳኮረፈ ውቃቢ ቀስ ብሎ ከዜጎች ዝጅመውታቱ አይቀርም።

በምትኩም ባርነትና ተገዢነት ቦታቸውን ይይዛሉ።ይህ ትውልድ እንደ ተረት እሰማው ሀገራችንን የማታት ፍርዓት እውን እየሆነና እየተቃረበ መጥቷል።ወቅቱ ሀገር በጣር የተያዘችበትና ህልውናዋ አደጋ ላኢ የወደቀበት ነው።በመሆኑም የሀገራችንን መከራና ችግር ተካፍለን ልንታገልላት ይገባል እንጂ የማናገኘውን የቅንጦት ህይወት የምንመኝበት መሆን የለበትም።

ፖለቲካን ጠላሁ በሚል ከሃላፊነት መሸ ሽ ዌኢም ሀገር በእሳት ስትነድ ባዕድ መጥቶ ያጠፋዋል በሚል ጭፍንአስተሳሰብ የምንጓዝበት ወቅት ላይ አይደለም ያለነው። ስለዚህ ትግሉ የሚጠይቀውን መስዋዕትነትን ለመክፈልየምንዘጋጅበትና በጋራና በተባበረ ክንድ ትግላችንን የምንቀጥልበተ ጊዜ ነው።

በጋራ በመታገል ሀገራዊ ግዴታችንን እንወጣ

By Tewodros Webeshte ቴዎድሮስ ውብሸት Germanyወያኔ ኢህአዴግ ዜጎችን በጣላትነት በመፈረጅ በዜጎች መካከል የጠላትነት መንፈስ እየፈጠረ ያለ መንግስት ነው።ወያኔ በእርሱ ትዕዛእ እንዲተዳደሩ ብቻ ሳይሆን እርሱ ራሱ ቢያምንበትም ባያምንበትም ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ዜጎች በእርሱ ሀሳብ ብቻ እንዲመሩ እያደረገ ነው።በዚህ ቅጥ ባጣውና ውሉ ባለየለት ሃሳቡም ሆነ በዚህ አሰራሩ ማመዛዘንና ማስተዋል የማይችሉ ብዙ ሆዳሞችንና የስርዓቱን አምላኪዎች ከጋራ ጥቅም ይልቅ የግል ጥቅማቸውን የሚያሳድዱ አድር ባዮችን ፈጥሯል።የኢህአዴግ ህገ መንግስት ብዙ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን ቢያካትትም የኢህአዴግ ባለስልጣናት ህገ መንግስቱን ባያከብሩ አያስገርምም።ህገምንግስቱ የተቀረፀው በወንጀለኞችና ለወንጀለኞች ስለሆነ ማለትም ስልጣን ላይ ባሉ ግብራበሮች ይሁንታ ስለሆነ አሁንም ወንጀል መፈፀማቸውንና ሰብአዊ መብት ረገጣቸውን ከመቼውም ጊዜ

Kendil January ,2014 First Year No.4 17

በላይ ቀጥለውበታል።ከኢህአዴግ ወያኔ ነፃ ሆነው በሙያ ማህበራትና በፖለቲካ አርቲነት ለመደራጀት ሚሞክሩ ዜጎች በአገዛዙ ይዋከባሉ።እንቅስቃሴያቸውም ይገታል።አባላትን በማፈንና ደጋፊዎቻቸውንና ህይወታቸውን ለነፃነታቸው ዋስትና እንዲያጡ ይደረጋል።ህይወታቸው የተቀጨም አለ።አገዛዙ ህዝብን እያሸበረ አሸማቆና አፍኖ ስለሚያዝ ተቃዋሚዎች ፣ጋዜጠኞችና የህዝብን መብቶች ለማስከበር የሚሞክሩ ህዝባዊ የሲቪክ ድርጅቶች ላይ እየፈፀመ ያለው ኢ ሰብአዊ ግፍና ፣ ግድያና እስር በዓለም አቀፍ ደረጃ በጥብቅ የሚያስወግዛቸውና የሚያስጠይቃቸው መሆኑ ግልፅ ነው።ባጠቃላይ በዚህ አምባገነናዊ ስርዓት በዘረፋ የበለፀጉ የስርዓቱ ተከታዮች ደጋፊዎች ሲሆኑ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ተጠቃሚ አይደለም።አብዛኛው የከተማ ነዋሪ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ በሄደው ኑሮ ውድነት እየተሰቃ ነው።አርሶ አደሩ የማዳበሪያ እዳ መክፈል አቅቶትታል።በብዚ ሺህ የሚቆጠር የሀገሪቱ የተማረ የሰው ሀይል ለስደት ተዳርጓል።በተለያዩ የ ዓለም ሀገራትና የአረብ ሀገራት የግፍና የውርደት ሰለባ ሆኗል።በመጨረሻም ወያኔ ኢህአዴግ ለፈፀማቸውንና እየፈፀማቸው ያለውን ወንጀል በመገንዘብ የሀገራችንን አንድነት ለማስጠበቅና ለማጠናከር ከመቼውም ጊዜ በላይ በበለጠ በአንድነትና በጋራ በመታገል ሃላፊነታችንን እንወጣ።

የጋራ ጠላታችን ህወሓት/ ኢህአዴግ ነው መአዛ ሳጂ ጀርመን

በአገራችን ያለው አስከፊ ሁኔታ እጅግ ተባብሷል:: ህወሓቶች ከመቼውም ጊዜ እጅግ በከፋ ሁኔታ በህዝቡ ላይ መጠነ ሰፊ ግፍን እየፈጸሙ ናቸው ይህንን ሁኔታ ለመቀየር ኢትዮጵያውያን አሁን እያደረግን ያለነው ትግልበቂ አይደለም :: ይልቁንም መከራውን ተለማምደን መከራ እጣ ፋንታችን እስከሚመስል ድራስ አብረነው ለመጓዝ የቆረጥን እንመስላለን :: ይህ ማለት ዛሬ መወሰን ካልቻልን የህወሃትን የጭቆና ቀንበር ተሸክመን ለመጓዝ መምረጣችን ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለትውልዳችንም ቢሆን ቀላል አይደለምና ይህንን ለመቀየር ጊዜው ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው:: ሁሉም የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ሁሉ የሚችለውን ማድረግ ያለበትን ማድረግ ይጠበቅበታል:: ህወሃቶች በየትኛውም ዘመን ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ህዝቡን በማሰቃየት ቀጥለውበታል:: ማንም መብቱን ለማስከበር ተፈጥሮአዊ ፣ አለምዓቀፍና የአገራችን ህጎች ቢፈቅዱልንም ህወሓት መብታችንን ገፎ ለመቀጠል ወስኗል:: ይህ ጉዳይ በአገራችን ህዝብ ህይወትና የየእለት እንቅስቃሴ ተገድቦ መኖር ግዴታ ሆኗል:: የተቀዋሚው ጎራም በአገር ውስጥም ሆነ በውጭው የምንኖረው ትግላችን ከህወሓት ጋር መሆን ሲገባው እርስ በዕርስ መስማማት ሳይታይባቸው በመቅረቱ በአንድ ላይ ሆኖ መታገል ሲገባ ትግሉን በመነታረክና ባለመስማማት ውጤታማ የሆነን ትግል ባለምድረጋቸው ዛሬ ኢትዮጵያውያንን ለትልቅ ሰቆቃ ተጋልጠናል :: ዛሬ የኢትዮጵያውያን ችግር በጋራ ሆነን መታገል ባለመቻላችን ህወሃት ዛሬ በህዝቡ ላይ ግፍ መፈጽሙን ቀጥሎበታል:: ይህንን የህዝባችንን ችግር ለመቀየር ያስችል ዘንድ ምንም ጥያቄ ውስጥ በማይገባ መልኩ የህወሃት ሥርዓት ከኢትዮጵያውያን ላይ በየትኛውም የትግል መንገድ ማስወገድ ይጠበቅብናል :: ስለሆነም በመካከላችን ያሉትን ልዩነቶችን ወደኋላ ብለን ትግሉን መግፋት ይጠበቅብናልና ዛሬ ነገ ሳንል ትግሉን በማቃጣጠል ህወሓትን መደምሰስ ይኖርብናል :: ለዚህም ደግሞ የተቀዋሚው ሃይል ትግሉ በከፍተኛ ሁኔታ መምራት ይኖርበታል :: እንግዲህ ትግሉን ለማገዝ ያስችለን ዘንድ የጋራ ጠላታችንን ማወቅ ይኖርብናል እሱም ሕወሃት በመሆኑ ይህንን በዝባዥና አንባገነን ሥርዓት ለመደምሰስ ቆርጠን እንነሳ:: በጋራ ጠላታችን በህወሃት/ ኢህአዴግ ላይ በጋራ እንነሳ !

የኢትዮጵያ ሴቶች ወደ ትግል እንቀላቀል

By አዳነች ተከተል ሸንኮር/ Adanech Teketel Shenkorጀርመን/ Germanyበአገራችን ባለው የፖለቲካ ጫና ምክንያት ከመቼውም ጊዜያት በላይ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ለከፍተኛ ችግርከመዳረጋችንም በላይ የሥርዓቱ ቀጥተኛ ተጠቂዎች ለመሆን ተገደናል:: ሥርዓቱ የህወሓት/ ኢህአዲግ

Kendil January ,2014 First Year No.4 18

መንግስት በወረቀት ብቻ ያስቀመጠው ህገ መንግስት ለሴቶችና ለህጻናት ከፍተኛ መብት ቢሰጥም በአገሪቷውስጥ በአሰፈነው አንባገነን ሥርዓት ምክንያት ሴቶች ለከፍተኛ የፖለቲካ፣ የማህበራዊና የኢኮኖሚ ጥቃቶችተጋልጠን እንገኛለን::በአገራችን በከፍተኛ ቁጥር ላይ የምንገኘው ሴቶች በምናደረገው ተሳትፎ ያሰጋውየህወሃት ሥርዓት ሴቶች ያላቸው ከፍተኛ ቦታ ያሰጋው በመሆኑና በራሱ የህወሓት የትግል ወቅት ኢትዮጵያውያንሴቶች ያደረጉት አስተዋኦ ቀላል እንዳልሆነ በመረዳቱ ከወንዶች በበለጠ የሴቶችን እንቅስቃሴ ለመገደብከምንም በላይ ተግቶ እንደሚሰራ የህወሃት የ 22 ዓመታቶች በግልጽ አሳይተውናል::ዓለም ለሴቶች መብትመከበር ከፍተኛን ትግል በምታደርግበት ጊዜና የዓለም ሴቶች መብታቸውን ለማስከበር ተጨማሪ ትግልንበሚያደርጉበት ወቅት በአገራችን እኩልነቱ ቀርቶ በሰብአዊ መብቶቻችን ላይ እየተደረጉ ያሉት ረገጣዎችከመቼውም የአገራችን አገዛዝ ዘመኖች ሁሉ የከፋ ጊዜ ላይ እንዳለን አሁን በአገራችን የሚታዩት ሁኔታዎችግልጽ አመላካቾች ናቸው::ከላይ ለጠቀስኳቸው ሁኔታዎች ለማሳያነት ያህል በፖለቲካው ዘርፍ በብርቱካንሚደቅሳ ላይ የተደረገው የፖለቲካ እንቅስቃሴ እገታና ተጽዕኖ በዓለም ህዝብ ጥረት ባይፈታ ኖሮ እየተፈጸመባትየነበረው ቀላል አይደለም:: ዛሬ ደግሞ ጋዜጠኛና መምህርት በሆነችው ርዮት አለሙ ላይ እየተፈጽመ ያለውግፍ አሁንም ቀጥሏል እንዲህ አይነቱ ግፍ በመላው አገሪቷ በከፍተና ሁኔታ በልዩ ልዩ ስፍራዎች በስውር በብዙሴቶች እህቶቻችን ላይ እየተፈጸመ እንደሆነ የታወቀ ነው::

ምክር ለህወሓት/ ኢህአዴግ መከላከያ ሠራዊት

ኤልሳቤጥ ሙላቱ ሐይሌ/ Elsabeth Mulatu Haileጀርመን / Germany

ባለፉት ዘመናት በአገራችን እንደታየው ከሆነ በኢትዮጵያ ወታደራዊው ኃይል በጥቂት የገዢ መደብ የብዝበዛናየጭቆና መሣሪያነት እያገለገሉ ቆይቷል:: ይሆንና ያሁኑን ገዢ ሥርዓት ከቀድሞዎቹ ጋር ስናነጻጽር ቀደም ሲልየተዋቀሩት የወታደራዊ ኃይሎች ከልዩልዩ ብሄረሰቦች የተዋቀሩ ከመሆናቸው በላይ ኢትዮጵያዊ አመለካከትእንዲኖራቸው ተደርጎ ኢትዮጵያን ከውስጥና ከውጭ ጠላቶች ሲመክት ቆይቷል::ዛሬ ግን የአገራችንየመከላከያ ሠራዊት የሌላት በመሆኑና በኢትዮጵያ መከላከያ ሥም ህወሓትን የሚጠብቅ ወታደራዊ መዋቅርበአገሪቷ ተዋቅሮ ህዝቡን በማስጨነቅና ለህወሓት የጭቆና መሣሪያነት እያገለገለ ይገኛል::ይህ የኢትዮጵያንሥም ይዞ ለህወሃት ለጭቆና አገልጋይ የሆነው ሠራዊት የሚቀርበውን ትጥቅና ሥንቅ የሚያገኘው ደግሞከኢትዮጵያን ገቢ ከሚሰበሰብ ታክስና ቀረጥና ከውጭ ኃይሎች በኢትዮጵያውያን ሥም በብድርና በዕርዳታከሚገኝ ገንዘብ መሆኑ ግልጽ ነው :: ነገር ግን አገልግሎቱን የሚሰጠው የኢትዮጵያን ህዝብ ለማስጨነቅናለግፍ መሣሪያነት ከመሆኑም በላይ በውጭው አገራትም እየተላኩ በሠላም አስከባሪነት ሥም አገረቷንለተቆጣጠሩት የህወሃት ጀነራሎች የኪስ ማደለቢያነትና የበዝባዦች መሣሪያነት አገልጋይ ሠራዊት ሆኗል::

ጭቁን ኢትዮጵያዊ ሆናችሁ የኢትዮጵያን ህዝብ ከሚያደማ የህወሓት ጀነራሎች ጋር ወግናችሁ ህዝብንየምታደሙ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የሆናችሁ ሁሉ ከዚህ በኋላ የህዝባችንን እንባ ለማበስ ቆርጣችሁየምትሰለፉበትና የህዝቡን ትግል ከዳር ለማድረስ ከህዝቡ ጋር ልትወግኑ የሚገባችሁ ሰዓት ነውና ከነጻነትታጋዮች ጋር እንድትቀላቀሉ ጥሪዮን አቀርባለሁ ::ይህ ካልሆነ ግን ታሪክ ሊፋረዳችሁ በህዝብ ላይምለፈጽማችሁትም ግፍ ከተጠያቂነት እንደማታመልጡ ከወዲሁ ልታውቁ ይገባችኋል እላለሁ ::

ከነዚህ ዘረኛና አፋኝ አንባገነን ሥርዓት አራማጆች እራሳችሁንና አገራችሁን ነፃ ለማውጣት መቁረጥ ያለባችሁጊዜ ነውና አብረን እንነሳ እራሳችሁን ከህወሓት ዘረኛ ቡድን አግልሉ:: ከዚህ በኋላ ከህወሃት መከላከያሠራዊትነት ይልቅ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ሆናችሁ አገራችሁን እንድትጠብቁና ከነዚህ አንባገነንጀነራሎች እጅ ህዝቡን እንድትታደጉ እመክራለሁ ::

እናንተ ይህን ባተደረጉ የነፃነት ታጋዮች ግን እናንተን ድል ለማድረግ መቁረጣችንን እንድታውቁ ይሁን ::ድል ለኢትዮጵያ ውድቀት ለህወሓት አንባገነኖች ይሁን ! ዘሬ የአገራችን ሴቶች በአገራችን ባለው የኢኮኖሚ መድሎ ምክንያትም በተለያየ አገራት ሴቶች እህቶቻችንተሰደው እንዲኖር በመደረጉና በየአረብ አገራቱ እየደረሰባው ያለው መከራ ከመቼውም ጊዜ በላይ የከፋ

Kendil January ,2014 First Year No.4 19

ለመሆኑ አሁን በሳውዲ አረቢያ የተፈጠረውን ሁኔታ በማየት ብቻ የሴቶች እህቶቻችንን ችግር መገመትይቻላል::ይህ ብቻ አይደለም ይህ ስርዓት ይዞት ባለው የፖለትካ ተጽዕኖ ምክንያት የአገሪቷ ኢኮኖሚበህወሃቶች እጅ የወደቀ በመሆኑና ሌሎች የአገራችን ሴቶች የአገርቷ የኢኮኖሚም መብትም ተጠቃምምባለመሆናቸውም ጭምር በአገራችን እየተፈጸመ ላለው የኢኮኖሚ፣የማህበራዊና የፖለቲካ መድሎዎችተጠቂዎች እየሆንን ያለነውም በቅድሚያ እኛው ሴቶች ነን::ስለሆነም ይህንን ሁኔታ ለመለወጥና የአገራችንየሰብዓዊ መብቶች መከበርና የማህበራዊ፣ የኢኮኖሚያዊና የፖለቲካ መብቶች ተከብረው ለማየት የሴቶችተሳትፎ ጉልህ ድርሻ ካልያዘ የአገራችን ሁኔታ እጅግ ወደከፋ ሁኔታ እየሄደ በመሆኑ ሁላችንም በተለይም ሴቶችለአገራችን የፖለቲካ ሁኔታ መቀየር ያለን አስተዋጾ ቀላል ባለመሆኑ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረግ የሚኖርብንበመሆኑና የመብቶቹም ተጠቃሚ እንድንሆን ያስችለን ዘንድ ከመቼውም ጊዜ በላይ ወደ ትግል ተቀላቅለንየትግሉ አካል እንድንሆንና ይህንን አስከፊ ዘረኛ ሥርዓት ማስወገድ ይኖርብናል::ስለሆነው የአገሬየኢትዮጵያ ሴቶች በትግሉ ውስጥ ቀጥተኛ ተሳታፊ በመሆንና መስዋዕትነትን በመክፈል አገራችንን ከጨቋኞችእጅ እናላቅቅ:: በዚህም የአገራችንን ሴቶች መጺሃ እድል በትግላችን እናረጋግጥ::

ወያኔ በሴቶች ስም መነገዱን ያቁም

By Ruta Abebe Münnerstadt

በኢትዮጵያ ሴቶች ግማሹን የህብረተሰብ ክፍል ይሸፍናሉ።ሀገራችን ለምታስቀምጣቸው የእድገት ዕቅዶችየሴቶች ሚና ከፍተኛ እንደሚሆን ምንም ትርጥር የለውም።ይሁንና አምባገነኑ መንግስታችን በወረቀት ሴቶችመብቶቻቸው ተከብሮላቸዋል እያለ ቢያወራም በተጨባጭ የሚታየው እውነታ ግን ከዚህ በተቃራኒው ነው።

በፍትህ እጦት፣በሀገር ውስጥ የስራ ዕድል ባለማግኘትና በህብረተሰቡ ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ እጅግ ዝቅተኛበመሆኑ የተነሳ በርካቶች እህቶቻችን ስደትን የመጨረሻው አማራጭ አድርገዋል።በርካቶች እህቶቻችን በተለይወደ መካከለናው ምስራቅ ሀገራት አካላቸውንና ነብሳቸውን መስዋዕት በማድረግ ያለማቋረጥ ይጓዛሉይሰደዳሉ።ይሁንና የእህቶቻችን ስደት በስቃይና በመከራ የተሞላ ነው።

በየእለቱ ከወደ መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ሚሰሙት አሳዛኝ ዜናዎችም ለዚህ ትልቁ ማረጋገጫናቸው።በቅርቡ እንኳን በሳውዲ አረቢያ እህቶቻችን በደህንነት ሀይሎችና በሀገሪቱ ወጣቶች ሲደበደቡ በጠራራፀሀይ ሲደፈሩና በዚህ ዘመን ለእንስሳት እንኳን በማይመጥን መልኩ በየጎዳናው ታርደው ሲጣሉ ተመልክተናል።ሴት እህቶቻችን ለዚህ ሁሉ አደጋ የተጋለጡት በሀገር ውስጥ በስራና በሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቾችሊኖራቸው የሚገባውን ፍትህ በመነጠቃቸው ነው።እናም ዛሬ በሌሎች ሴቶች እህቶቻችን ላይ እያየነውናእየሰማነው የሚገኘው ይህ አሳዛኝ እውነታ ነገም በኛው ስለሚሆን እኛ ሴቶች መብቶቻችንን ለማስከበር በጋራእንታገል።

የኢትዮጵያ ህዝብ በፃነት ለማስከበር በጋራ እንነሳBy waleligne Zerga DeguMünnerstadt

በተለይ ከ 1997 ምረጫ በመለስ የኢትዮጵያ ህዝብ በርካታ መብቶቹን ተነፍጓል።የሲቪክ ማህበራትየመደራጀት መብታቸውን በአፋኙ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ህግ ተነጥቀዋል።መገናኛ ብዙሃን አዲስ በወጣውመገናኛ ብዙሃንና የመረጃና ነፃነት በሚለው አዋጅ እንቅስቃሴያቸው ተገድቧል።ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችናመገናኛ ብዙሃንን ጨምሮ የፀረ ሽብር አዋጅ በሚለው ህግ እስከ ወዲያኛዉ በፃነታቸውን ተነጥቀዋል።የእነኚህሁሉ ህጎች ጠንሳሽ የሆነው ኢህአዴግ በአሁኑ ወቅት በምክር ቤቱ ከአንድ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት ጋር ብቻነው የሚከራከረው።የመናገርና የማሰብ ነፃነትን የሚከለክሉት እነኚህ ህጎች የህዝባችንን ተፈጥሯዊ ሰብዓዊመብቶች የገደቡ ናቸው።እናም ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶቻችንን ለማስመለስ ሁላችንም በየተሰማራንበት

Kendil January ,2014 First Year No.4 20

መስክ መታገል ይኖርብናል። ለመብቶቹ መከበር ያልተንቀሳቀሰ መብቶቹን ማስከበር አይችልምና በተለይ በዚህዘመን የምንገኝ ወጣቶች ሀገራችንንና ህዝባችንን በሚመለከት ትልቅ ሀላፊነት አለብንና ለትግሉ በጋራ እንነሳ !

የአንድነታች ጠላት የሆነውን ወያኔን ለመጣል እንታገልHanna Yosef nigusse

Münnerstadt

የሀገራት ታሪክ የተዘበራረቀ ነው።በአሁኑ ወቅት በእድገት ማማ ላይ የሚገኙት ሀገራት ታሪክም ቢሆን በበጎናበመጥፎ ጎኖች የታጀበ ነው።ማንም ሀገር አንድ ወጥ ጥሩና በጎ ታሪክ ይዞ እዚህ የደረሰ የለም።

ቀደምት የሀገራችንን ታሪክ የተመለከትን እንደሆነ ሀገሪቱን ያስተዳድሩ የነበሩ መንግስታት የሀገራችንን አንድነትለማስጠበቅ የተለያዩ ስልቶችንና መንገዶችን ተጉዘዋል።ተጠቅመዋልም።

በተለይ ከ 1983 ዓ.ም በሃላ ማለትም ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣበት ወቅት አንስቶ ግን በአንድነቷየምትታወቀው ሀገራች በዘረኛውና በአምባገነኑ የወያኔ ስርዓት የተለያዩ ፈተናዎች አጋጥመዋታል።

ከፈተናዎቹ አንዱ ታሪክን እያንሻፈፉ ወቅታዊ ለሆኑ ክስተቶች በብሔርና ዘረኝነትን ፅንፍ ማስተርጎምናየሚፈጠረውን ክርክር በጥላቻ ጥቁር ቀለም መቀባት ነው።

ወያኔ ኦሮሞውን ከአማራው ለማጋጨት የተለያዩ ጥረቶችን አድርጓል እያደረገም ነው።የሀገሪቱን ታሪክ በብሔር የነፃነት ጥያቄዎች ዙሪያ ብቻ እንዲያጠነጥኑ ለማድረግ መገናኛ ብዙሃንንና ሌሎችገለልተኛነትና ነፃነት የሚገባቸው መድረኮችን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል።በዚህ አፈና የጨዋታውን ሂደት በማን እንደሚመራ ለማወቅ ብዙም አስቸገሪ አይሆንም።

እናም አሁን ሀገራችን ያለችበትን የታሪክና የአንድነት አደጋ በመረዳት ሁላችንም የአንድነት ጠላት የሆነውንወያኔን እንታገል።

ኢትዮጵያዊነት ይቅደም!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

ለሀገራችን የመረጃ ነፃነት ትግል እናድርግ

ፋንታ አዳነ ደሳለውMünnerstadt

የመረጃ ነፃነት ዲሞክራሲያዊ የሆነ ማህበረሰብን ለመፍጠርና ለመገንባት ከፍተኛ ሚና የሚጫወት መሆኑ አያጠራጥርም። በመረጃ የተገነባ ማህበረሰብ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚኖረው የወሳኝነት ሚና ሚዛናዊነትንና ትክክለኛነትን የተላበሰ ነው። የመረጃ ነፃነት ግልፅነትና ተጠያቂነት የሚሰማውን ማህበረሰብ በመፍጠርም ሚናውየጎላ ነው። ሚዛናዊና ትክክለኛ ያልሆኑ ውሳኔዎችን መከላከል የሚቻለውና ግልፅነትና ተጠያቂነት የሚሰማውን ማህበረሰብ መፍጠር የሚቻለው ደግሞ ያለ ማንኛውም አካል ጣልቃ ገብነት የሚንቀሳቀሱ መገናኛ ብዙሃን ሲኖሩ ነው። የመረጃ ነፃነትን የሚፈጥሩ የተለያዩ ተቋማት ቢኖሩም ከእነኚህ ተቋማት መካከል በዋናነትና በይበልጥ ተጠቃሹ የመገናኛ ብዙሃን ተቋም ነው። ከዚህ በተቃራኒው ግን አምባገነን መንግስታት ግልፅነትና ተጠያቂነትን ለመሸሸግና የስልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም በመጀመሪያ የሚወስዱት እርምጃ መገናኛ ብዙሃንን በቁጥጥር ስር ማዋል ነው። መገናኛ ብዙሃንን በቁጥጥር ስር ያዋለ መንግስት በሌሎች ተቋማት ላይ የሚኖረው ተፅህኖ እጅግ በጣም የጎላ ነው። በዚህ ረገድ አምባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት በዋናነት ተጠቃሽ ነው። አምባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ በመገናኛ ብዙሃን ላይ የተለያዩ ዘመቻዎችን ከፍቶ ተቋማቱን አቅም በማሳጣትና በማሽመድመደ ላይ ይገኛል። ባለፉት ሁለት አስርት

Kendil January ,2014 First Year No.4 21

አመታት ተከፍተው ያልተዘጉ ጋዜጦችና መፅሔቶች የሉም።በርካታ ጋዜጠኞች ከመንግስት በሚደረግባቸው ዘመቻ ሀገር ጥለው መሰደድን መርጠዋል። በሀገር ውስጥ ያሉ መገናኛ ብዙሃን ቢሆኑም መንግስት በተለያየ መልኩ ጣልቃ እየገባባቸው ተግባራቸውን በአግባቡ እንዳይወጡ የተለያዩ ተፅህኖዎችን እያደረገባቸው ይገኛል።በተለይ በኢትዮጵያ የሚገኙ የሀገራችን ህዝቦች መረጃ የሚያገኙበት ምንጭ የጠበበና በአሁኑ ወቅት ምንም አይነት ሚዛናዊ መረጃ የሚያገኝበት ዕድል የተዘግጋ ነው። ስለሆነም የህዝባችን ዲሞክራሲያዊ ሂደት ለማፋጠንናሀገራችንን ወደምናልምበት ደረጃ ለማድረስ ለመረጃ ነፃነት መከበር ሁላችንም በያለንበት ትግል እናድርግ!

ሰላማዊ ሰልፍ በባዕድ ሀገራት እና“አስራ አንደኛው ቀን” በሳውዲአረቢያ

በውቤ አለማየሁከጀርመን

በሳውዲ አረቢያ በወንድምና እህቶቻችን ላይእየተፈፀመ ያለውን አሰቃቂ ግፍና መከራለመቃወም ህዳር 5 ቀን 2006 ዓ.ምበጀርመን ፈራንክበርት ሳውዲ አረቢያ ቆንስላበተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተገኝቼነበረ።በሰልፉ ለይ ለመሳተፍ በኢትዮጵያየሰዓት አቆጣጠር ከለሊቱ አስራ አንድ ሰዓት ነበርወደ ባቡር ጣቢያው ያመራነው።በለሊትየተነሳንበት ዋነኛ ምክንያት ሰልፉን በጠዋትለመጀመር ዕቅድ በመያዙ ነው። እኔ ካለሁበትአካባቢ በርካታ ቁጥር ያላቸውኢትዮጵያውያን ወንድምና እህቶቼም ተሳታፊዎች ነበሩ።እለቱ በሳውዲ አረቢያ በምስኪኑ ህዝባችን ላይ መፈፀም የጀመረው ግፍና መከራ “አስረኛውን ቀን” ያስቆጠረበት ነበር።በእነኚህ አስር ቀናት የሰው ልጅ ደም በየሜዳው እንደ ጎርፍ ሲወርድ ፤አካሉ ደግሞ እንደ እንጨት ሲፈለጥና ሲቆረጥ አይተናል።በማህበራዊ ሚዲያዎች በኩል ከስፍራው የሚወጡ የቪዲዮና የፎቶ ምስሎች እንደሚያመለክቱት የሳውዲ አረቢያ ደህንነቶችና ወጣቶች እንዲሁም አሰሪዎች እህትና ወንድሞቻችን ላይ እጅግ ዘግናኝና አሳዛኝ ድርጊት ፈፅመዋል።አንዳንዶቹ “የድረሱልን ጥሪ” ሲያሰሙ ከልብ የሚያሳዝኑና የሚያስለቅሱ ናቸው።እንኳን አይደለም አስር ቀናት በመከራና በጭንቀት የሆነች አንዲት ደቂቃ ከዓመት ትስተካከላለች።ሰላማዊ ሰልፋችን በፍራንክፈርት ሳውዲ አራቢያ ቆንስላ ልክ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከጠዋጡ አራት ሰዓት ነበርየተጀመረው።በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ህፃናትን በመሸከሚያ ጋሪ የያዙ እናቶች፣ ወጣቶች ፣አዛውንቶችና የሀይማኖትአባቶች ሳይቀሩ በተለያዩ የጀርመን ግዛቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተገኝተው ነበር።በጀርመን ሀገር የሚገኙ ኤርትራውያን ወንድሞቻችን በሰልፉ ላይ የኢትዮጵያና የኤርትራን ባንድራ በመያዝ “እኛ ኤርትራውያን በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርገውን በደል እንቃወማለን ” የሚል መፈክር አሰምተዋል።ዘር፣ሀይማኖት፣ ብሔርና የፖለቲካ አስተሳሰብን ሳንለይ ሁላችንም ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ወንድሞቻችን ኤርትራውያን በሳዉዲ አራቢያ ቆንስላ የተገኘንበት ዋነኛ ዓላማ የሳውዲ አራቢያ መንግስትና ህዝብ በንፁሀን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ እየፈፀሙት የሚገኘውን አሰቃቂና ዘግናኝ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በፍጥነት እንዲያቆሙ ለመጠየቅ ነው። ከዚህ ባለፈ መስማት የተሳነውንና ዝምታን የመረጠውን አንባገነኑን መንግስት“በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ህዝባችንን ከመጨፍጨፍ እንዲያድንልን” ለመጠየቅ ነው። የሰላማዊ ሰልፍ ሁነቱንለመዘገብ በስፍራዉ ለሚገኙ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍና መገናኛ ብዙሃን ኢ-ሰብአዊ ድርጊቱ ሲፈፀምበዝምታ መመልከት ለመረጡት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና ባጠቃላይ ለዓለም አቀፉንማህበረሰብ እንዲያሳዉቁልን ለማድረግ በማሰብ ነው ።

ለሰላማዊ ሰልፉ ከተሰባሰብንበት መንገድ ፊት ለፊት አንድ ሰማይ ጠቀስ ህንፃ ይታያል። የህንፃው እያንዳንዱፎቅ ለተለያዩ አማካሪና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የተከራየ መሆኑን ህንፃው መግቢያ ላይ የተዘረዘሩት ፅሁፎችያስረዳሉ። የሳውዲ አረቢያ ቆንስላ በዚህ ሰማይ ጠቀስ በሆነው ህንፃ ሀያ አራተኛ ፎቅ ላይ ነው የሚገኘው።

Kendil January ,2014 First Year No.4 22

ሰላማዊ ሰልፋችን ከዚህ ሰማይ ጠቀስ ህንፃ ትይዩ ቢበዛ በአስር ሜትር ርቀት ላይ ተጀመረ። ሰላማዊ ሰልፉችን “ሰብዓዊነትንና የሀገር ክብርን” መሰረት ያደረገ በመሆኑ የሰላማዊ ሰልፉ ስሜት እየጋለ መጣ። ሁላችንም የሰልፉ ተሳታፊዎች ያች የሶስት ሺህ ዓመታት ታሪክ ባለቤት የሆነችው ሀገራችን ኢትዮጵያ በሳዉዲ አረቢያ “ንጉሶች” ስትደፈር ታየችን።የህዝባችን ሰቆቃና ጩሀት፣ መከራና እንግልት እያንዳንዳችን ላይ የተፈፀመ አድርገን አሰብነው። በእውነት ኢሰብአዊ ድርጊቱን ለመሸከም ይከብዳል።በአስር ሜትሮች ርቀነው የነበርነውን የሳውዲ አረቢያ ቆንስላ የሚገኝበትን ህንፃ መግቢያ ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጠርነው። የህንፃው መግቢያና መውጫ በሰልፉ ሙሉ ለሙሉ ተዘጋ።የህንፃው መግቢያ ላይ ደህንነት የሚያስጠብቁ ፖሊሶች ቢኖሩም ፖሊሶቹ ወደ ህንፃው ውስጥ እንዳንገባ ከመከልከል ውጭ ሰላማዊ ሰልፋችንን በሰላማዊ መንገድ እንድናደርግ ሙያዊ ሃላፊነታቸውን ከመወጣት ውጭ ሰላማዊ ሰልፉን በትዝብት ይመለከቱ ነበር።ሰላማዊ ሰልፉ ቢያንስ ለሶስት ሰዓታት ተደርጓል። በዚህ እለት በተመሳሳይ ሰላማዊ ሰልፎች በመላው አውሮፓ በእንግሊዝ ሎንዶን፣በሲውዲን ስቶኮልምና በሌሎች የአውሮፓ ዋና ዋና ከተሞች እንዲሁም በአሜሪካን ዋሽንግተን ዲሲ ይደረግ ነበር።በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በዓለማችን ዋና ዋና ከተሞች ሰላማዊ ሰልፉ ሲደርግ በኢትዮጵያ የሚገኙ ወገኖናችን ግን በመንግስት ክልከላ ምክንያት በሀገር ቤት የሳውዲ አረቢያ መንግስትን ድርጊት ማውገዝ አልቻሉም።

አስራ አንደኛዉ ቀንይህ እለት በሳውዲ አረቢያ ያለው ሰቆቃና ኢ-ሰብአዊ ድርጊት አስራ አንደኛ ቀኑን የያዘበት ነው።ይህ እለት ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ ሳውዲ አረቢያ ኤምባሲ ሰላማዊ ሰልፍ የጠራበት እለት ነው ።ሰላማዊ ሰልፉ ከሚደረግበት ሳውዲ አረቢያ ኤምባሲ አካባቢ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ግን በአምባገነኑ መንግስት የሚታዘዘው የደህንነት ክፍሉና ፖሊሶች በሰልፊ ተሳታፊዎች ላይ ከባድ ድብደባና እስራት በመፈፀም ሰልፉ እንዲበተን አድርገዋል።አሶሺየትድ ፕሬስየኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ዴታን ሽመልስ ከማልንጠቅሶ እንደዘገበው ሰልፉ የተበተነው “ሰልፈኞቹ ሰላማዊሰልፍ እንዲያደርጉ ስላልተፈቀደላቸው ነው” ።ሽመልስእንዳለው “ሰልፈኞቹ ሳውዲ አረቢያ ላይ ጥላቻየሚፈጥሩ መልዕክቶችን በመያዛቸውና እነኚህመልዕክቶችም ኢትዮጵያ ከሳውዲ አረቢያ ጋር ያላትንየጠበቀ ግንኙነት የሚያሻክር በመሆኑ ነው” ብሏል።ሰማያዊ ፓርቲ በበኩሉ “የኢትዮጵያ መንግስት ከሳውዲ አረቢያመንግስት ጎን በመቆም ዋና ተባባሪ መሆኑንአስመስክሯል” ሲል ባውጣው መግለጨ የአምናገነኑንኢህአዴግ መንግስት ድርጊት አውግዟል።በሀገር ቤት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሳውዲ አረቢያኢ-ሰብአዊ ድርጊትን በሰላማዊ ሰልፎች መቃወምናሰላማዊ ሰልፎችንም በሀገራችን ማድረግ አልቻሉም።ወገናችን ለተፈፀመበት ግፍና ሰቆቃ ህዝባችን በሀገሩመጮህ ተልክሏል። አምባገነኑ መንግስታችን ሰላማዊሰልፍ “በባዕድ ሀገራት ከተሞች እንጂ በኢትዮጵያአታደርጉም፤አትችሉምም ” ብሎናል።መንግስትተብዬው ኢህአዴግ በሀገራችን ባዳ አድርጎናል።መንግስታችን በሀገራችን ባዳ ሲያደርገን በሌሎች የዓለማችንዋና ዋና ከተሞች የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ግን በትውልድ ሀገራችን ማድረግ ያልቻለውን ሰላማዊ ሰልፍ በባዕድሀገራት ማድረግ ችለናል። በዚህም ምክንያት እኛ ኢትዮጵያውያን “ሰላማዊ ሰልፎችን በባዕድ ሀገራት ብቻእንድናደርግ ነው እንዴ የተፈርደብን? ” ብዬ እንድንጠይቅ ተገደድኩ። ቢፈረድብንስ …..ግን ፍርዱእስከመቼ?

Kendil January ,2014 First Year No.4 23

ከገፅ 10 የቀጠለ ….የማንዴላ መንግድ

ማንዴላ በኢትዮጵያ ቆይታቸው የስድስት ወራትወታደራዊ ስልጠና ያደርጋሉ ተብሎ የታሰበ ቢሆንምከደቡብ አፍሪካ ውጭ ሰባት ወራትን በመቆየታቸውከፓርቲያቸው በተደረገላቸው የአስቸኳይ ጥሪ ብዙምሳይቆዩ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።ማንዴላ ወደሀገራቸው ከመመለሳቸው አስቀድሞ ግን ጀነራል ታደሰብሩ አንድ ሽጉጥና 2 መቶ ቀለሀዎች በስጦታአበርክተውላቸው ነበር።እነኚህ የስጦታ መሳሪያዎችማንዴላ 18 ዓመታትን በእስር በቆዩበት ሮቢን ደሴትሊልስሊፈ ፋርም Lillesleaf Farm በተባለአካባቢ እንደተቀበረ ይነገራል።የኢትዮጵያ ቆይታቸውን በሚመለከት ማንዴላ በግለታሪከቸው ላይ"ኢትዮጵያ በውስጤ ልዩ ቦታ ያላት ሀገርነች።ሀገሪቱ በጥቅሉ ወደ ፈረንሳይ፣እንግሊዝና አሜሪካከማደርገው ጉዞ ይልቅ ትልቅ ግምት የምሰጠው ነው።ምክንያቱም ወደ ኢትዮጵያ የማደርገው ጉዞ አንድም ወደ ቀደምት የዘር ግንዴ እንደሄድኩ ስለሚሰማኝ በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያ አፍሪካዊ የመሆን መሰረቴ መገለጫ ስለሆነች ነው "ብለዋል።ማንዴላና አስተምዕሮዎቻቸውየኛን ሀገር ጨምሮ በተለይ በአፍሪካ አሁን ድረስ ብዙዎች የማንዴላም መንገድ መጋጓዝ የከበዳቸው ናቸው። እነኚሁ ሀገራት ከማንዴላ አስተምርዎች ብዙ መማር የሚኖርባቸው ቢሆንም አካሄዳቸውን ግን በሌላኛው መንገድ አድርገዋል። በካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨሪሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማሪያም በጦማራቸው እንዳስነበቡት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ከማዲባ የምንማራቸው በርካታ ቁም ነገሮችአሉ ታላቅ ህዝብ የመሆን ጠንካራ ፍላጎት አንዳንድ ጊዜ በታሪክዊ አጋጣሚ ታላቅ ህዝብ የመሆን ካባ አንድ ትውልድ ላይ ይወድቃል። ይህ እኛ የምንገኝበት ወጣቱ ትውልድ የዚህ ታሪክ ቀያሪ የለውጥ ካባ ለባሽ ልንሆን እንችላል።የሁሉም የሆነች አንዲት ኢትዮጵያን ለመፍጠር ማንዴላ የቀድሞው ያረጀውና ያፈጀው የመጠላላትናየመፈራራት መንገድ በይቅር ባይነትና በህርቅ አዲሱ መንገድ መቀየሩን እንደሚኖርበት ያስተምሩናል።

ማንዴላ በአንደበታቸው እንደተናገሩት "ከነጮቹ ጋር ድርድር በምናደርግበት ወቅት አንድ የተማርኩት ቁም ነገር ቢኖር እኔ የግል አስተሳሰቤንና አመለካከቴን እስካልቀየርኩ ድረስ የሌሎችን አስተሳሰብና አመለካከትን መቀየር እንደማልችል ነበር" ብለዋል። በመሆኑም እኛ ወጣቶች በተለይ የጥላቻ መንፈስን ለራሳችን ህልውና ስንል ከውስጣችን ማስወገድ እንዳለብን ነግረውናል። "ጥላቻ አንተ መርዝ ጠጥተህ መርዙ ጠላቴን ይገልልኛልብለህ ተስፋ እንደማድረግ ነው" ሲሉም ገልፀውታል። ማንም ሰው ከጥላቻ ጋር እንዳልተወለደ የሚናገሩት ማንዴላ ሰዎች ጥላቻን ከሌሎች እንደሚማሩት ነው የሚገልፁት። ሰዎች ጥላቻን በትምህርት ካዳበሩት በምትኩ በተፈጥሮ አብሮን የተፈጠረውን የፍቅርና የመተሳሰብ አመለካከትንም እንዲሁ ብንማረው ፍቅርና ይቅር ባይነትን ይበልጥ ልናዳብረውና ልናሳድገው እንደምንችልም ገልፀዋል። ያለማቋረጥ የሚደረግ ጥረትማንዴላ ለኛ ለወታቶች የዘር፣የሀይማኖትና የቋንቋ ልዩነቶች ከእያንዳንዳችን የፀጉር ቀለም ያልተለየ ምንም ፋይዳ እንደሌለው ነግረውናል እናም ዓላማችንን ለማሳካትና የምናልማት ኢትዮጵያን እውን ሆና ለማት ያለማቋረጥ ጥረት ማድረግ እንዳለብን አስተምረውናል።ማንዴላ ፍትህና ትክክለኛነት እንደ ጅረት ውሃ ያለማቋረጥ እየወረዱየምናይበት ጊዜ እስኪመጣ ድረስ ያለማቋረጥ ጥረት ማድረግ እንዳለብን ነገረውናል።ማንዴላ "እኔን መለካት የሚኖርባቹ በስኬቶቼ ብቻ ሳይሆን ዓላማዬን ለማሳካት ስንት ጊዜ ወድቄ ስንት ጊዜ እንደተነሳሁ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። ዓላማን ለማሳካት ውድቀት ቢኖርም ጥረታችንን ካላቋረጥን ግን

ከውድቀታችን መነሳት የምንችልበት ዕድል እንዳለ ነው የሚገልፁልን፡፡ ስህተቱ ውድቀት ሳይሆን ደግሞ አለመሞከር ነው ውድቀት።ማንዴላ "በህይወት የመኖር ትልቁ ትርጉም መውደቅ አለመቻል ሳይሆን በእያንዳንዱ አጋጣሚ ከውድቀታችን መነሳት መቻላችን ነው" ብለዋል።አንዱን አቀበት ስትወጣው ልሎች ብዙያልተወጡ አቀበቶች አሉ ስኬት መጨረሻ እንደሌለውም ነገረውናል ።

Kendil January ,2014 First Year No.4 24

መተባበር እንደሚኖርብንማንዴላ እኛ ወጣቶች የምንወዳት ሀገራችንን እውን ሆና ለማየት መተባበር እንደሚኖርብን ነግረውናል።ማንዴላ"አንድ ግለሰብ ብቻውን ሀገርን ነፃ አያወጣም።ሀገርን ነፃ ማውጣት የሚቻለው ተባበረው ከሰሩ ብቻ ነው "በሚለው ንግግራቸው ይታወቃሉ።>ለራስ መታመን የሞራል ልዩ ብቃት ነው። ለራስ መታመን ማንም የሚመከለት በማይኖርበት ወቅትም ቢሆን ትክክለኛውን ነገር መፈፀምና ለመፈፀም ሁል ጊዜ ጥረት ማድረግ መቻል ነው። ማንዴላ "ደጋግሜ እንደተናገርኩት የመጀመሪያው ነገር ለራስ መታመን ነው" ብለዋል።በመጀመሪያ ራሱን ያልቀየረ አንድ ግለሰብ በማህበረሰቡ ውስጥ በጎ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብሎ ማሰብ እንደማይቻልም ነግረውናል ።ጀግናነትማንዴላ ጀግና በመሆን አምነው ጀግና ሆነው አልፈዋል። ማንዴላ "እኔ ራሴን ሁል ጊዜ የአፍሪካ ጀግና አድርጌነው የማስበው "ይላሉ። የአፍሪካ ጀግኖች ቀኝ ግዛትን አስወግደዋል።የደቡብ አፍሪካ ጀግኖች ደግሞ የአፓርታይድ ስርዓትን ያለአንዳች ደም መፋሰሽ ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለውጠዋል።ከዚህ የምንማረው ኢትዮጵያውያን ወጣቶችም ለህዝባችንና ለአህጉራችን ጀግና መሆን እንዳለብን ነው ። የኢትዮጵያ ጀግኖች ደግሞ ድህነትን፣ቸልተኝነትንና አምባገነንነት በማስወገድ የምንወዳት ኢትዮጵያን የመገንባት ሃላፊነት አለብን።ደፋር መሆን እንዳለብንማንዴላ "እኔ እንደተረዳሁት ደፋርመሆን የፍራቻ አለመኖር ሳይሆንፍራቻን ማሸነፍ መቻል ነው" ብለዋል።አክለውም "ደፋር ሰው የፍራቻስሜት የማይሰማው ሳይሆን ፍርዓቱንየሚቆጣጠራት ነው" " ሲሉምአስረድተዋል።እናም እኛ ወጣቶችየምንወዳትን ሀገራችንን ለመፍጠርፍራቻን ማሸነፍ የሚችል ደፋር መሆንእንዳለብን ነው።ሩቅ አላሚነትማንዴላ "እኔ እራሷ በራሷ ሰላምየሆነች አፍሪካን አልም ነበር " ብለዋል። ያይዘውም " ስለ ውብደቡብ አፍሪካ ህልሞች ካሉን ደግሞወደዚያ ግብ የሚያደርሱን መንገዶችአሉ ማለት ነው። ከእነኚህ መንገዶችሁለቱ መልካምነትና ይቅርባይነትናቸው" ሲሉ ተናግረዋል።እኛኢትዮጵያውያን ወጣቶችምየምንወዳት ኢትዮጵያን እውን ሆናለማየት ሩቅ ማለም ይኖርብናል።የማህበረሰባችን መሰረቶች ደግሞ ሰላም፣አንድነትና ተስፋ መሆን ይኖርባቸዋል።ከሃላ መምራትማንዴላ በተለይ ስኬትን በምንቀናጅበት ወቅት ሌሎችን ከፊት በማስቀደም ከሃላ ሆኖ ሌሎችን መምራት ከፍተኛ የአመራር ጥበብ መሆኑን ያስረዳሉ።አደገኛ ሁኔታ በሚያጋጥምበት ወቅት ደግሞ ከፊት መቅደም የበሳል አመራር ባህርይ መሆን እንዳለበት ያስረዳሉ።በዚህ ወቅር ሰዎች አመራርህን ያደንቃሉ።ከሃላ ሆኖ በመምራት ብዙዎች ከፊት እንዳሉ እንዲያምኑ የሚያስችላቸው በጎ ስነልቦናዊ አስተዋፅኦ እንዳለውም ይታመናል። "እረኛከሃላ ሆኖ ከብቶቹን ይነዳል።ከከብቶቹ መካከል አንዱ ይቀድማል። ሌሎችም ይከተሉታል።ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ሁሉም ከብቶች ከሃላ በአንድ እረኛ ወደ አንድ መስመር እየተመሩ እንደሆነ አይገነዘቡም" ሲሉ በአንድ ወቅት ተናግረዋል ።እናም ማንዴላ የምናልማትን ሀገራችንን ለመመስረት ይህንን የአመራር ጥበብ ከውስጣችን ማኖር ይኖርብናል።ማንዴላ ስለአመራርነት የሚናገሩትና አድርገው ያሳዩትም አንድ የአመራር ጥበብ አለ "አመራርነት መልቀቅም አመራርነት ነው"

ፍርደኛ መሆንን መጠበቅማንዴላ እኛ ወጣቶች የምናልማትን ሀገራችንን ለመገንባት ስንል ፍርደኞች ልንሆን እንደምንችል ይግልፃሉ።

Kendil January ,2014 First Year No.4 25

እኛ ወጣቶች ዓላማችንን ለማሳካት ስንል ህገወጦች እንደምንባል፣ብዙዎች እንደሚያንጓጥጡንና ሰብአዊ ክብራችንን እንደሚደፍሩ ገልፀዋል።በመጨረሻ ግን አሸናፊዎች እኛ አንደምንሆን ነው የገለፁት። ማንዴላ "እኔትላንት አሸባሪ ተብዬ ነበረ። ከእስር ስፈታ ግን አሳሪዎቼን ጨምሮ ብዙዎች ተጠመጠሙብኝ ።አሁን ለሌሎች የምናገረው ነገር በሀገራቸው ለነፃነት የሚታገሉ የነፃነት ታጋዮች አሸባሪዎች እንደሚባሉ ነው"ብለዋል።ከጠላት ጋር ሰላም መፍጠርማንዴላ እኛ ወጣቶች ለሃገራችን ሰላም ስንል ጠላቶቻችንን መቅረብ፣ቀርበንም እጆቻቸውን መጨበጥ ከዚያም አልፈን አቅፈን ልንስማቸው እንደሚገባ ይነግሩናል። ማንዴላ "ከጠላቶቻችሁ ጋር ሰላም መፍጠር ከፈለጋችሁ ከጠላቶቻችሁ ጋር መስራት ኢኖርባችዋል።ከዚያም ጠላቶቻችሁ አጋሮቻችሁ ይሆናሉ" ብለው ነገረውናል።ድህነትን መዋጋት እንደሚኖርብንማንዴላ"ድህነትን መወጋት የበጎአድራጎት ስራ ሳይሆን ፍትህን የማስፈህ ተግባር ነው።ልክ እንደ ባርነትና አፓርታይድ ስርዓት ሁሉ ድህነትም ተፈጥሯዊ አይደለም። ድህነት ሰው ሰራሽና በሰዎች መልካም ተግባር ሊወገድ የሚችል ነው "ብለዋል።ስለዚህም እኛ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ድህነትን በመዋጋት ሰው ሰራሽ የሆነውን ማህበራዊ ኢፍትዓዊነት መዋጋት አለብን ። ሀገራችንንም ከዚህ ማህበራዊ ኢሰብአዊነት ማዳን ይኖርብናል። ምክንያቱም ድህነት ልክ እንደ ባርነትና አፓርታይድ ስርዓት ሁሉ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ወንድምና እህቶቻችንን ሰለባ እያደረጋቸው ነው። በመርህሆች ላይ አለመደራደርማንዴላ "እኔ ዘርንና ቀለምን መሰረትያደረገ አድሎንና መገለጫዎቹንእጠላለሁ።ለዚህም ህይወቴን በሙሉተዋግቼለታለሁ። አሁንም እየተዋጋሁኝነው ።የህይወቴ መጨረሻ እስኪመጣድረስም እዋጋለታለሁ " ብለዋል።ማንዴላ ይህንን ፈፅመውታል።እኛየኢትዮጵያ ወጣቶችም የምንወዳትሀገራችንን ለመፍጠር መሰረታዊመርሆዎች ላይ መደራደርአይኖርብንም።በዘር ጭቆና፣ማንነትመሰረት ባደረገ ፖለቲካ፣ በብሔርክፍፍል፣በፆታ ጭቆና፣ በኢኮኖሚብዝበዛና በማህበራዊ አድሎዎች ላይየማይናወጥ አቋም ሊኖረን እንደሚገባንመክረውናል።ቀና አሳቢ ተስፈኛና ወሳኝነት

ማንዴላ "በተፈጥሮም ይሁን በትምህርትአላውቅም እኔ ግን ቀና አሳቢነኝ"ብለዋል።ቀና አሳቢ የመሆን አንዱመገለጫ አስተሳሰብ ደግሞ አሉ ማንዴላ"ምልከታን ወደ ፀሀይ መውጫ አቅንቶእግርን ደግሞ አንድ እርምጃ ወደፊትማራመድ ነው" ብለዋል።"የሰብአዊነትትግሌን በሚመለከት በርካታ ጨለማ ታሪኮች ቢኖሩም ራሴን ግን ተስፋ ለማስቆረጥ አልፈለግኩምም አልቻልኩምም። ተስፋ መቁረጥ መሸነፍንና ሞትን ይወልዳልና" ብለዋል።እኛ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችም የምናልማትህ ሀገራችንን ለመፍጠር ተስፈኛ መሆን ይኖርብናል።ምክንያቱም የኢትዮጵያ ጥሩ ቀኖች የመምጫጊዜ ወደፊት ነውና።እናም እኛ አፍሪካውያን ወጣቶች ማንዴላ ያሳኩትን አድርገነው ለማየት ከፈለግን እንደማንዴላ ረጀሙን ጉዞ መጓዝና እንደማንዴላ ጠንካራ መሆን ይኖርብናል። መማርና ማስተማርማንዴላ "ትምህርት ዓለማችንን ለመቀየር የምንጠቀምበት ትልቁ መሳሪያ ነው።ማንም ሀገር ያልተማረ ዜጋ ይዞ ያደገ የለም " ሲሉ ተናግረዋል። ገለልተኛ አለመሆንኢፍታዊነትንና ሴጣናዊ ተግባርን በሚመለከት ገለልተኛነት ልንሆን አይገባም። ከሴጣናዊ ተግባር ይበልጥ

Kendil January ,2014 First Year No.4 26

ሴጣናዊ የሚሆነው ለሴጣናዊ ተግባር ገለልተኛ መሆን ነው።ሴጣናዊ ተግባር በማንናውም መልኩ ተቃውሞ ሊደረግበት ይገባል።ማንዲላ "እኔ አንድ ምትሃታዊ ማሳያ የለኝም። አልነበረኝም። ይልቁኑም እኔ በሺዎች የሚቆጠሩ ብስጭቶች፣ ተቃውሞዎችና እለት እለት በውስጤ ያደሩት ብሶቶች ናቸው ለዚህ የትግል እልህ ያነሳሱኝ" ብለዋል።ማንዴላ "ህዝቤን ነፃ ለማውታት ከዛሬ ህይወቴን ሰጥቻለሁ ብዬ የወሰንኩበት ቀን አልነበረኝም።ይልቁኑም እኔ ራሴን ሆኜ አገኘሁት እንጂ" ብለዋል።ይቅር ባይነትማንዴላ በ 1990 ለ 27 ዐመታት ታስርውባት ከነበረው እስር ቤት ተለቀው ሲወጡ አንድ ያስተላለፉት መልዕክት አለ"ከእስር ተፈትቼ እርምጃዎቼን ነፃነት ወደማገኝበት የእስር ቤቱ ደጅአፍ ሳደርግ በአንድ ነገር እርግጠኛ ነበርኩ። እርሱም የጥላቻና የበቀል በጥፎ ስሜቶቼን ወደ ሃላ ትቻቸው ካልወጣሁ አሁንም እስር ቤት እንዳለሁ መሆኔን ነው"።

የማንዴላ ዓመታት

1918 በምስራቃዊ ኬፕ ሞቬዞ በተባለች ግንቦት 18 ቀን ተወለዱ1943 አፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስን ተቀላቀሉ የፖለቲካ እንቅስቃሴያቸውን በያፋ

ጀመሩ1956 በከፍተኛ የሀገር ክህደት ተከሰው ክሱ ካዓራት ዓመታት በሃላ ውድቅ

ተደረገላቸው1962 በፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለው ሰዎችን ለአመፅ በማነሳሳትና ያለፓስፖርት

ከሀገር በመውጣት በሚል የዓምስት ዓመት ፍርድ ተላለፈባቸው1964 መንግስትን ለመጣል አሲረዋል በሚል የእድሜ ልክ ፍርድ ተላለፈባቸው

1990 ለ 27 ዓመታት ከታሰሩበት እስር ቤት ተለቀቁ1993 የዓለም የሰላም የኖቤል ተሸላሚ ሆኑ

1994 በደቡብ አፍሪካ የተደረገውን ምርጫ በማሸነፍ የደቡብ አፍሪካየመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ

1999 ከአመራርነት በፈቃዳቸው ለቀቁ

Kendil January ,2014 First Year No.4 27

“During my lifetime I have dedicated myself to this struggle of the African people. Ihave fought against white domination, and I have fought against black

domination. I have cherished the ideal of a democratic and free society in whichall persons live together in harmony and with equal opportunities. It is an ideal

which I hope to live for and to achieve. But if needs be, it is an ideal for which I amprepared to die.”

“As I walked out the door toward the gate that would lead to my freedom, Iknew if I didn't leave my bitterness and hatred behind, I'd still be in prison.”

Kendil January ,2014 First Year No.4 28